በኢንተርኔት ልጆችን በቤት ውስጥ  ማስተማር የሚያስችል የዩቲዩብ ቻናል ተከፈተ

የኮረና ቫይረስ በመላው ዓለም መስፋፋቱን ተከትሎ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው በቤት ውስጥ መዋል ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች ትምህርቸውን በኢንተርኔት አማካይነት እንዲማሩ እንቅስቃሴዎች የተጀመሩ ሲሆን እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ደግሞ ከገፅ ለገፅ የትምህትር አሰጣጥ ጎን ለጎን በኢንትርኔት አማካይነት ትምህርን ለማስጀመር መንግስት እቅድ ነድፏል፡፡

ነዋሪነቷን በአሜሪካ ያደረገችው የህፃናት መፅሀፍት ደራሲ ሶፊያ ፀጋዬ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት በሚሄዱበት ወቅትም ሆነ በኢንተርኔት አማካይነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ወላጆች ልጆቻቸው እንዴት መርዳት እንዳለባቸው የሚመከር የዩቲዮብ ቻናል የከፈተች ሲሆን በርካታ ወላጆች ቻናሉን እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡

<4 ኪሎ የሚገኘው የአርበኞች ማህበር ህንፃ ሊፈርስ ነው>

ሶፊያ ከዚህ በፊት ሶስት የህጻናት መፅሐፍትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተመች ሲሆን የመጀመሪያው   She is my mommy የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን ስለ ማደጎ ልጅ ታሪክ የሚተርክ ነው፡፡ ሁለተኛው Your jokes are not funny የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን በተለይም ህፃናት ባለመጠንቀቅ የሚቀልዷቸው አጉል ቀልዶች እንዴት የሌሎችን ህጻናትን ስሜት እንደሚጎዱ የሚያስተምር ነው፡፡  your third eye is cool የተሰኘው ሶስተኛው መጽሀፏ ደግሞ የተለየ ልዩ ፍላጎት ይዘው የሚወለዱ ልጆች ያ ልዩነታቸው የሚያሳፍር ሳይሆን የእነርሱ የተለየ ጸጋ መሆኑን ተቀብለው ከሌሎች ህፃናት ጋር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያስተምር መፅሐፍ ነው፡፡

የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ሶፊያ  ከልጆቿ ዕድሜና የትምህርት ደረጃ ተነስታ በሶስት ደረጃ የተከፈለ የሪሞት ለርኒንግ ትምህርት አሰጣጥ ስልትን በማቅረብ  ወላጆች ልጆቻቸው ሊያስጠኑ እንደሚችሉና የንባብ ልምዳቸውን በቀላሉ ሊያዳብሩ እንደሚችሉ ትገልፃልች፡፡

<በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ድንበር አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ላይ ምርመራ እየተካሄደ…>

ዕድሜያቸው  ከ 3 ዓመት   እስከ  7 ዓመት ለሆናቸው፤ ከ7  ዓመት እስከ 13 ዓመት ለሆናቸውና ከ14 ዓመት እስከ 18 ዓመት ለሆናቸው ተማሪዎች እንዴት በቤት ውስጥ በኢንተርኔት አማካይነት ልጆችን እንዴት መርዳት እንደሚቻል በየሳምንቱ ምክረ ሀሳብን ትሰጣለች፡፡

የሶፊያን ምክሮችና  ትምህርቶች መከታታል የሚፈልጉ ወላጆች www.youtube.com/Sophia Tsegaye በሚለው የዩቲዩብ ቻናል ገብተው መከታታል እንደሚችሉ ሶፊያ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፃለች፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe