እስራኤል ኦፕሬሽን ኢትዮጽያ ስትል በጠራችው አዲስ ዘመቻ በርካታ ኢትዮጽያዊያን ተጠቃሚ ሆነዋል ተባለ፡፡
እስራኤል በተለያዩ ጊዚያት ኦፕሬሽን ኢትዮጽያ በሚል የጤና ቡድኖችን ወደ ኢትዮጽያ በመላክ የነጻ የህክምና አገልግሎት ስትሰጥ መቆየቷን በአዲስ አበባ የእስራኤል አምባሳደር ከ1ወር በፊት ከቁምነገር ሚዲያ ጋር በነበራቸው ገልጸው ነበር፡፡
ከሰሞኑም በእስራኤል የህክምና ቡድን በተሰጠ የዓይን ህክምና የብዙ ኢትዮጽያዊያን ብርሃን ተመልሷል ነው የተባለው፡፡
በፕሮፌሰር ሞሪስ ሃሪስተን የተመራው የህክምና ቡድን በደሴ ከተማ ቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል ነጻ የዓይን ህክምና አድርጓል፡፡
ይሔው የእስራኤል የህክምና ቡድን 530 ለሚሆኑ ኢትዮጽያዊያን ከቀላል እስከ ውስብስብ ደረጃ የደረሱ የዐይን ቀዶ ጥገና ማድረጉ ነው የታወቀው፡፡
ይህ እስራኤል ኦፕሬሽን ኢትዮጽያ ስትል የምትጠራው ዘመቻ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ድርሻው ከፍ ያለ እንደሆነ ይነገራል፡፡
እስራኤል ከጤናው ዘርፍ ባሻገር በግብርና፡በቴክኖሎጂ እና ባህል ዙሪያ ከኢትዮጽያ ጋር በቅርበት የምትሰራ መሆኗን አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ንጉሴ ለሚዲያችን መግለጻቸውም ይታወሳል፡፡

