በእነ ስብሃት ነጋ መዝገብ 113 የምስክርና በርካታ ማስረጃ መሰብሰቡን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፡- እነ ስብሃት ነጋ ለሦስተኛ ጊዜ በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።ፖሊስም በእነ ስብሃት ነጋ መዝገብ 113 የምስክርና በርካታ ማስረጃ መሰብሰቡን አስታውቋል።

ፖሊስ፣ እነ ስብሃት ነጋ ትናንት ለሦስተኛ ጊዜ በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ወቅት እንዳስታወቀው፤ በእነ ስብሃት ነጋ መዝገብ 113 የምስክርና በርካታ ማስረጃ ሰብስቧል።

በትናንትናው የችሎት ውሎ ፍርድ ቤቱ የእነ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር አባይ ወልዱና ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ የተመለከተ ሲሆን፤ ችሎቱ በማይካድራ በንጹሐን ግድያ ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 36 ተጠርጣሪዎችን ጉዳይም በተጨማሪነት ተመልክቷል።

እነ ስብሃት ነጋ እና ሌሎች የህወሓት አመራሮች፣ የጦር መኮንኖችና ሌሎችም ግብረአበሮቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በተለያየ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል።

አዲስ ዘመን የካቲት 6/2013

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe