በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 500 ሚሊዮን ሰዎች ወደ አስከፊ ድህነት ወርደዋል ተባለ

ኮቪድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተ ወዲህ የሰዎች የዕለት ተዕለት ግንኑነት ተስተጓጉሏል፤ ስራ ቀዝቅዟል፤ ኢኮኖሚ ተዳክሟል፤ በመሆኑም ሳይሰሩ የሚበሉ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ኑሮ ተወዷል፤

የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት ግማሽ ቢሊዮን ህዝብ ወደ አስከፊ ድህነት ወርዷል፡፡

መንግስታት እና ተቋማት ትኩረታቸውን ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራዎች በማድረጋቸው ምክንያት ሌሎች ስራዎች እየተረሱ እንዲመጡ ማድረጉንም ድርጅቱ ገልጿል፡፡

አሁን ላይ በወባ እና ቲቢ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ከ10 ዓመት በፊት ወደነበረበት በመመለስ ላይ ነውም ተብሏል ድርጅቱ፡፡

ኮሮና ቫይረስ በመከሰቱ እና የተለያዩ የጉዞ እቀባዎች በመደረጋቸው ቱሪዝምን ጨምሮ ሌሎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለው ብዙዎች ወደ ድህነት እየወረዱ መሆኑን የዓለም ባንክ ገልጿል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe