የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ማሕበርን በማቋቋም ከ1988 እስከ 1992 በፕሬዚዳንትነት የመሩት እና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ውስጥ በአማካሪነት የሠሩ ሲሆን፤ 2007 ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከበክኔል ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል። ከወረርሽኑ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ጉዳት እስከምን ሊዘልቅ ይችላል? በሚል እና በሌሎችም ከኢኮኖሚው እና ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ በኢኮኖሚው ዘርፍ ስላስከተለው ተፅእኖ የኢዜማው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዕለታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
Read also:የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ አስተናጋጆች ለመስጠት የወሰነው የቋንቋ ፈተና ተቃውሞ ገጠመው
አዲስ ዘመን፡- አፍሪካ በኮቪድ-19 ከተጠቁ አህጉራት የመጨረሻዋ ስትሆን፤ አገራቱ ትምህርት ቤት መዝጋት፣ በተወሰነ መልኩ ዜጎቻቸው ከቤት ውጭ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፣ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ የማስቀመጥ ርምጃዎችን እየወሰዱ ነው።በኢትዮጵያም እነዚህ እርምጃዎች እየተወሰዱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ከበሽታው ጋር በተያያዙ የተለያዩ ምክንያቶች ወረርሽኙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ምን ያህል ነው?
ፕሮፌሰር ብርሃኑ፡- በአጠቃላይ በእንዲህ ዓይነት ወረርሽኝ ወይም በሌላ ምክንያት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ወትሮ ከሚሄዱበት ፍጥነት እና ጥንካሬ ባነሰ እንዲሄዱ ሲደረጉ እንደተለመደው በምርት እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በጣም ብዙ መቀነስ እና ጉዳት ይዘው ይመጣሉ።ይህ ትልቅ ሳይንስ የሚፈልግ አይደለም።ሰዎች የሚያመርቱት ሥራ ሲሄዱ ብቻ ነው።ሰዎች መገበያየት የሚችሉት ከቤት ሲወጡ ነው።መምህራን የሚያስተምሩት ልጆች ትምህርት ቤት ሲሄዱ ነው።ሰዎች ከቤታቸው ሲወጡ እና ሲገቡ የትራንስፖርት አገልግሎት ይኖራል።
Read also:የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎቹን በዚህ ዓመት እንደማያስመርቅ አስታወቀ።
ይህ ሲቀንስ የአገር ኢኮኖሚ ይጎዳል።ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ሲቆም፤ የቱሪስት እንቅስቃሴ በዛው ልክ ይቀንሳል።የቱሪስት እንቅስቃሴ ሲቀንስት ከቱሪስት የሚጠቀሙ የኢኮኖሚ አካላት ከሆቴሎች ጀምሮ እስከ አስጎብኚዎች፤ የመኪና አከራዮች እና ተያያዥነት ያላቸው አካላት በሙሉ ችግር ውስጥ ይገባሉ።በወረርሽኙ ሳቢያ ይህ መሆኑ የማይቀር ነው።
እንዲህ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲመጣ ‹‹የኢኮኖሚ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል›› በሚል የሚመረጠው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ማከናወን ነው? ወይስ የሰው ህይወት ማዳን ነው? ሲባል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውም የሰውን ህይወት ለመጠበቅ እና ለመታደግ እስከሆነ ድረስ የሰውን ህይወት የሚያጠፋ አደጋ ሲመጣ ቅድሚያ የሚሰጠው የሰውን ህይወት ለመቅጠፍ የመጣን አደጋ መከላከል ነው።
አዲስ ዘመን፡- የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለው ችግር ምን ያህል የተወሳሰበ ይሆናል?
Read also:በኢትዮጵያ በአራት አመት ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ዕቅድ መኖሩን ጠቅላይ…
የኢኮኖሚ ተፅዕኖ በእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ ዝቅተኛ ሆኖ ከቀጠለ ጥሩ፤ ነገር ግን በእርሻው ላይም እየሰፋ ከሄደ ርሃብ ሊያጋጥም ይችላል።ስለዚህ የሚወስነው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚጠፋው ጊዜ፣ ያለው መስፋፋት ምን ያህል ነው? የሚነካቸው የኢኮኖሚ ክፍሎች ምን ያህል ናቸው? የሚለው ነው።ይህንን ደግሞ ብዙ ጊዜ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሞዴል እየሰሩ የሚያጠኑ አካላት ሊሆን ይችላል ወይም በተወሰነ መነሻ መላምት ላይ ተመስርተው እያጠኑ ነው። ያ መላምት ላይሆን ይችላል።መጀመሪያ ‹‹በጣም ብዙ ሰው ሊሞት ይችላል›› ተባለ ብዙ ሰው አልሞተም።‹‹ኦ በጣም የሚሞተው ሰው ቁጥር ይቀንሳል›› ሲባል ደግሞ መጨመር ጀመረ።ስለዚህ አይታወቅም።
በኢትዮጵያም የኢኮኖሚክስ ማህበር ሁለት እና ሶስት የሚሆን መላምቶች ላይ ተነስቶ በማጥናት፤ በጣም ቶሎ ብዙም ሳይስፋፋ በሽታው በኢትዮጵያ የመቆያ ጊዜው ካበቃ እስከ 2 ነጥብ 2 በመቶ ዓመታዊ ምርት ሊቀንስ ይችላል። በወር ደግሞ እስከ 10 በመቶ ምርቱ ሊቀንስ ይችላል፤ ቢባልም በእርግጠኝነት ማውራት እና ማለት አይቻልም።በእርግጠኝነት ማለት የሚቻለው ጉዳዩ ከቆየ ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ እና እንድምታው እየከፋ ይሄዳል የሚለው ነው፡፡
Read also: ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክያት ከ139 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ባለይ የሚገመት…
ሌላው የተጠቂዎቹ ብዛት እየሰፋ እና እየጨመረ ከሄደ የሚነካቸው ዘርፎች እየጨመረ ይሄዳል።ስለዚህ አደጋው ይከፋል። ነገር ግን ተወደደም ተጠላ አሁን እንዳለው ዝቅተኛ ሆኖ ቢቀጥል እንኳ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተወሰነ ደረጃ ከውጪው ኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ ሌላው ዓለምም ሁኔታው ተሻሽሎ የውጪ ንግድ እንቅስቃሴው በፊት በነበረው መልኩ እስከሚደርስ ድረስ ህዝቡ እንደበፊቱ መንቀሳቀስ እስከሚጀምር እና ቱሪስቶች ያለፍርሃት መንቀሳቀስ እስኪጀምሩ ድረስ በሚቀጥለው አንድ ዓመት ድሮ እንደነበረው ቦታ ለመመለስ ይቻላል የሚል እምነት የለኝም።