በወራት ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ የተደረገው የግብጽ እና የሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ተጠናቀቀ

የሃገራቱ ጥምረት ለኢትዮጵያ ስጋት ሳይሆን እንዳልቀረም ነው የተገለጸው፡፡

ልምምዱ ሃገራቱ ሊቃጣባቸው የሚችል ስጋትን ለማስወገድ ያለመ ነውም ተብሏል፡፡

ግብጽ እና ሱዳን ሲያደርጉ የነበረውን የጋራ የምድር፣ የአየር እና የባህር ኃይሎችን ያሳተፈ የጦር ልምምድ አጠናቀቁ፡፡

ስድስት ቀናትን የዘለቀው ወታደራዊ ልምምድ ካርቱም ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ሰፈር የተካሄደ ሲሆን ትናንት ሰኞ ነው የተጠናቀቀው።

የልምምዱን መጠናቀቅ አስመልክታ መግለጫ የሰጠችው ሱዳን ልምምዱ “የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናከር በዘለለ በጋራ ሊቃጣባቸው የሚችል ስጋትን ለማስወገድ ያለመ ነው” ስትል አስታውቃለች።

አሶሼትድ ፕሬስ ልምምዱ የሁለቱን ሀገራት የደህንነት ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ሀገራቱ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ለገቡት ውዝግብ ኃይላቸውን ለማሳየት የተጠቀሙበት ነው ሲል ዘግቧል፡፡

በልምምዱ መቋጫ ስነ ስርአት ወቅት የሱዳኑ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሞሀመድ ኦትማን አል-ሀሴን እና የግብፁ አቻቸው ሌ/ጄ ሞሀመድ ፋሪድን ጨምሮ የሀገራቱ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

ሱዳን እና ግብጽ በተለይ የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ባልተለመደ ሁኔታ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ላይ ናቸው።

የናይል ንስሮች እና ጠባቂዎች በሚሉ ስያሜዎችም ተከታታይ ወታደራዊ ስልጠናዎችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይህ ትናንት የተጠናቀቀው የናይል ጠባቂዎች ወታደራዊ ልምምድ የናይል ንስሮች ቁጥር 1 እና 2 በሚል የተካሄዱት ልምምዶች ተከታይ ነው፡፡

የልምምዶቹ መከታተል ምናልባትም ለኢትዮጵያ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አንዳንዶች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

ከሚያዝያ ወር ወዲህ በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙርያ የሚደረጉ ድርድሮች ቢቆሙም በኢትዮጵያ በኩል የግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት በመጪው ክረምት ለመሙላት ዕቅድ እንደተያዘ ነው፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe