በዓለም ዙሪያ ባሉ በርካታ የሙዚቃ ኃያስያን እውቅናና አድናቆት ያገኙት ፒያኒስት እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ

የውብዳር ገብሩ | እማሆይ ጽጌ ማርያም | ፧፠፨፠፧
እኚህ ነበሩ … ነብስ-ኄር
የውብዳር ገብሩ እ·አ·አ ታኅሣሥ 12 ቀን 1923 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ተወለዱ።
አባታቸው ክንቲባ ገብሩ እና እናታቸው ካሳዬ ለምቱ ሁለቱም በሀገሬው የተከበረ ቦታ ነበራቸው። የውብዳር በስድስት ዓመታቸው ከእህታቸው ሰነዱ ገብሩ ጋር ወደ ስዊዘርላንድ በመጓዝ ቫዮሊንና ፒያኖ ወደሚያጠኑበት የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በመግባት ስለቫዮሊን ተምረው ሲጨርሱ አሥር ዓመትም አልሞላቸውም ነበር።
.እ·አ·አ በ1933 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በእቴጌ መነን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸውን ቀጠሉ። እ.ኤ.አ. በ 1937 የዉብዳርና ቤተሰባቸው በጣሊያን ጦር ተማርከው ከሰርዲኒያ በስተሰሜን ወደምትገኘው ወደ አሲናራ ደሴት እና በኋላም በኔፕልስ አቅራቢያ ወደሚገኘው መርኮሊያኖ ተወሰዱ።
ከጦርነቱ በኋላ የዉብዳር የሙዚቃ ትምህርታቸውን በካይሮ ቀጥለው ፤ አሌክሳንደር ኮንቶሮቪች በተባለ ፖላንዳዊ ቫዮሊስት መምህራቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ሲሆን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአስተዳደር ረዳት ሲሆኑ ኮንቶሮቪች በንጉሠ ነገሥት ጦር ጠባቂነት በአፄ ኃይለ ሥላሴ የባንዱ የሙዚቃ ዳይሬክተርነት ሆነው ተሹመዋል።
የውብዳር በ19 ዓመታቸው ከአዲስ አበባ በድብቅ ሸሽተው ወሎ ውስጥ ወደምትገኘው ግሸን ማርያም ገዳም ከእናታቸው ጋር በመሄድ በገዳሙ ለሁለት ዓመታት አገልግለው በ21 ዓመታቸው ምንኩስናን ተቀብለው እማሆይ የሚለውን ማዕረግ በመቀበል ስማቸው እማሆይ ጽጌ ማርያም በሚል ተቀየረ።
እማሆይ በሃይማኖታዊ ሥርዓት ውስጥ አስቸጋሪውን ሕይወት እና ለሙዚቃቸው ያላቸውን አድናቆት ሌት ተቀን በትጋት መሥራት ቀጥለው በቀን እስከ ዘጠኝ ሰአት በመጫወት ለቫዮሊን፣ ፒያኖ እና ኦርጋን የሚሆኑ ብዙ ድርሰቶችን ጽፈውም ነበር።
በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ እማሆይ በጎንደር የዜማና የማህሌት አባት የሆነውን ቅዱስ ያሬድ የጥንቱን የኢትዮጵያ ሀይማኖታዊ ዜማ ሲያጠኑ ኖሩ። በየእለቱ ወደ ቤተክርስትያን ሲሄዱና ሲመለሱ “የቆሎ ተማሪ” የቅዳሴ ትምህርት ቤት ወጣት ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ደጃፍ ውጪ ለምን እንደሚያድሩ ቢጠይቁ ትምህርታቸውን በቤተክርስቲያን ቅዳሴን ከዜማጋር ለመከታተል ሲሊ ምግብና ማደሪያ እየለመኑ ቤት አልባ እንደሆኑ ይነግሯቸዋል።
እነኚህ ወጣቶች ማህሌትን ለማጥናት በከፈሉት መስዋዕትነት እማሆይ በጥልቅ በመነካትም የምሰጣቸው ገንዘብ ባይኖረኝእንኳ በሙዚቃዬ ተጠቅሜ እነዚህንና ሌሎች ወጣቶችን ለመርዳት ቆርጠው መነሳታቸውን እማሆይ በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛ ሬዲዮ ፕሮግራም ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ለአሉላ ከበደ ተናግረዋል።
.የእማሆይ የመጀመሪያ አልበማቸው በጀርመን ሀገር እ·አ·አ በ1967 በአፄ ኃይለ ሥላሴ እገዛ ታተመላቸው። በእህታቸው ደስታ ገብሩ እርዳታም ሌሎች ቅጂዎች አሰረከትለው በተገኘው ገቢ በጦርነት ላይ ለሞቱት ወታደሮች ልጆች ማሳደጊያ አውለውም ነበር።
እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ የፒያኖ ድርሰታቸውን በ1973 አሳትመው ከሙዚቃቸው ሽያጭ ያገኟቸውን ገቢዎች በኢትዮጵያ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህፃናትን ተጠቃሚ አድርገዋል።
እማሆይ እናታቸው በ1984 ዓ.ም መሞታቸውን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ኢየሩሳሌም የተጓዙበት ምክንያት በአምባገነኑ መንግስቱ ሀይለማርያም ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ በነበረው የሶሻሊስት አስተምህሮ በሃይማኖታዊ እምነታቸው ላይ ጥቃት ቢሰነዘርባቸውም ነው።
እማሆይ 95 ዓመት አልፏቸውም ቢሆን በገዳሙ ውስጥ በቀን ለሰባት ሰዓታት ያህል ፒያኖ ከመጫወት ሳይቦዝኑ አዳዲስ የፒያኖ ሙዚቃዎችን መጻፋቸውን ቀጥለው በዓለም ዙሪያ ባሉ በርካታ የሙዚቃ ኃያስያን እውቅናና አድናቆት አግኝተው በ99 ዓመታቸው አርፈዋል።
፧፠፨፠፧ # MULER Design & ArtPhotographer MULER ፧፠፨፠፧

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe