በዓለም የጤና ድርጅት ”የኤስ ኤስ ኤ‘ የመረጃ ዳታ ኢትዮጵያን በተመለከተ ባዶ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኑም በዓለም የጤና ድርጅት አማካይነት ተፅእኖ ማድረጋቸው እንደቀጠለ ነው፤

የድርጅቱ  ”የኤስ ኤስ ኤ‘ የመረጃ ዳታ ኢትዮጵያን በተመለከተ ባዶ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ታላላቅ ከሚባሉት ዓለምአቀፍ ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡ ይሕ ዓለም አቀፍ ተቋም በየአገሩ በጤና ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እንዲመዘገቡ ብሎ በሥራ ላይ ያዋለው ‹‹Surveillance system for attacks on health care›› (SSA) የተሰኘ መተግበሪያ አለው። ይህ መተግበሪያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጭምር ዕውቅና የተሰጠው ነው፡፡

እኤአ በ2017 ይፋ የሆነው መተግበሪያው በህክምና ተቋማት ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ የሚረዳ ነው፣ በየአገሩ በጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን መዝግቦ ይይዛል፡፡ መረጃው ዓለም እንዲውቀው ለሁሉም ይፋ ይደረጋል፡፡

ማንኛው ግለሰብ፣ ድርጅት፣ አገርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሆነ ተመራማሪዎችም መረጃ በቀላሉ ማግኘትና እርዳታም ሆነ ጥናት ማድረግን ጨምሮ በሚፈልገው መልኩ በግብአትነት ሊጠቀሙበት ይችላሉ ፡፡

በየትኛው ጦርነት ሆን ብሎ የህዝብ አገልግሎት መስጫዎችን በተለይም የጤና ተቋማትን ማውደም የተከለከለ ነው፡፡ የጤና ተቋማትን ማውደም የጦር ስትራቴጂ ሳይሆን የጦር ወንጀል ነው፡፡ በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ነውረኛው አሸባሪው ሕወሓት በአንፃሩ ከዚህ እሳቤ ጋር ፈፅሞ የሚተዋወቅ አይመስልም ይላ ዕለታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ፡፡

ወትሮውንም የተዳከመ የጤና አገልግሎት ባለባት ኢትዮጵያ ለኅብረተሰቡ የጤና አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ላይ የተፈጸመው ዘረፋ፣ ውድመትና ጉዳት እጅግ አሳዛኝ ከመሆኑ ባሻገር በአሁኑ ወቅት በወራሪው ቡድን ተግባር የአካልና የስነ ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው ነፍሰጡር እናቶች፣ አረጋውያንና ህፃናት በተለይም ተከታታይ ህክምና የሚያሻቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ የጤና ችግር ተጋላጭ ሆነዋል፡፡

የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴርም ከቀናት በፊት ይፋ ባደረገው መረጃም በወረራ ቡድኑ ስር ቆይተው የመንግሥት ኃይሎች ዳግም በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ከ2 ሺ 700 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ተዘርፈውና ጉዳት ደርሶባቸው አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮጵያና ዜጎቿ በአሰባሪው ቡድን ጤና እና ጤና ተቋማቶቿን ተንጥቃ ወራትን ስትቆስል ብትቆይም ዓለም አቀፉ ተቋም ግን ይህን አላየሁም አልሰማሁም ብላል፡፡ ኢትዮጵያ ከመቀነቷ ፈትታ ባላት አቅም ሁሉ መንገድ አስይዛ የገነባችው የጤና ተቋማት በወራሪው ሀይል  ሲወድም ዝም የማለት ሞራል አግኝቷል፡፡

ዓለም አቀፍ ተቋም በየአገሩ በጤና ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እንዲመዘገቡ ብሎ በሥራ ላይ ያዋለው ››Surveillance system for attacks on health care››(SSA) በተሰኘው መተግበሪያ ላይ በኢትዮጵያ የደረሰው ጉዳትም አልተመዘገበም፡፡ ማንኛውም ሰው ወደ መተግበሪያው የኢትዮጵያን ስም ሲያስገቡ የሚመለከተው ቁጥር ዜሮ ነው፡፡ መረጃው ምንም አይነት ጉዳትም ሆነ ጥቃት የለም ይላል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ተቋማት እንዲስፋፉ እና ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እሰራለው የሚል ድርጅት፣ እንዴት በሺዎች የሚቆጠሩ የጤና ተቋማት ሲወድሙ፣ የመድሃነት መጋዘኖች ተዘርፈው ከጥቅም ውጭ ሲሆኑ ዝም አለ? እንዴትስ ማውገዝ ተሳነው? ጉዳቱስ እንዴት ሳይመዘገብ ቀረ ? ሊሆን ይችላል ? ብሎ መጠየቅ ደግሞ የጤናማ ሰው ተግባር ነው፡፡

መልሱ በጋራ ከሚሰሯቸው የዛሬዎቹ መሰል ድራማዎች ውስጥ በጉልህ ይታያል። ለእኔ ካለጥርጥር ሆን ተብሎ የእብሪተኛና አሸባሪን ቡድን ኢ ሰብአዊ ተግባራትን ለማድበስበስ የተሴረ ሴራ ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ዓለም አቀፉን ድርጅት የሚመራው ሰው፣ የጤና ተቋማቱን ባወደሙት አሸባሪዎች ወገን መሆኑ ነው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅትም የባለሙያነት ስነምግባርና መርህ አንጻር ማንኛውም ሰራተኛ በምንም መንገድ በአንድ ሃገር የፖለቲካ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይችልም፡፡ መሪውም ከዓለም ጤና ድርጅት ጥቅም ውጪ የሌላ አካል ጥቅም ለማስጠበቅ በምንም መልኩ መንቀሳቀስ አይፈቀድለትም፡፡

ይሑንና የትግራይ ክልል ተወላጁ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለመላው የዓለም ህዝብ ወኪል በመሆን የዓለም ጤና ድርጅትን በዋና ዳይሬክተርነት እያገለገሉ ቢሆንም ህግና ስነምግባርን ባልጠበቀ መልኩ ለአንድ በአሸባሪነት ለተፈረጀ ቡድን ሽፋን ለመስጠት ሲንቀሳቀስሱ ታይተዋል፡፡

ከሀኪም ይልቅ ፖለቲከኛ የሆኑት ሰው፣ የዓለም አቀፍ ተልዕኮ ዕድልን ተጠቅሞ የሕወሓትን ጁንታን ለመርዳት ሲያደርጉ የሚታየው ጥረት እንደ አንድ የዓለም ዓቀፍ ድርጅት መሪ ሳይሆን ወገንተኛነት የተጫነው የአንድ ቡድን አክቲቪስት መምሰል ከጀመረም ውሎ አድሯል።

በዚህ ተግባራቸውም በመንግስት ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለማሳደር የቡድኑን ጥፋት ለመሸፋፈንና ነፍስ ዘርቶ እንዲመጣ ለመደገፍ ሲፍጨረጨሩ ታዝበናቸዋል፡፡ ለዚህም ሰውየው ባለፉት አንድ አመት በግል የማህበራዊ ገጻቸው ላይ የሽብር ቡድኑን የሚደግፍና በትክክልም የቡድኑ አባልና ደጋፊ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጡና የኢትዮጵያን መንግስት ለመወንጀል የተቀመሩ መልዕክቶችን በተደጋጋሚ ማጋራታቸውን በቂ ምስክር ይሆናል፡፡

በጣም የሚያስገርመው ደግሞ ሰውየው ትግራይ ክልል ሲሆን ሁሌም ያሳስባቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም‹‹ሰዎች በረሃብ ምክንያት እየሞቱ ነው፤ የጤና አገልግሎት ተቋማት ወድመዋል፥ አስገድዶ የመድፈር አድራጎት በብዛት እየተፈጸመ ነው ሲሉ አድምጠናል።

በትግራይ ክልል በርካቶችም እየሞቱና አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የሚነግሩን ሰው፣ የሽብር ቡድኑ ባለፉት ወራት በወረራ ይዟቸው በቆያቸው የአፋርና የአማራ ክልል ስለፈጸመው ኢ ሰብአዊ ድርጊትና ድርጊቱ ስለተፈፀመባቸው ንፁኃን ትንፍሽ አይሉም፡፡

በሚያሳዝን በሚያሳፍርና በሚያስቆጣ መልኩ በሽብር ቡድኑ አባላት ንፁሃን ዜጎች ሲገደል፣ ሲደፈርና የጤና ተቋማት እንዳልነበር ሲወድሙ አይተው እንዳላየ ሰምተው እንዳልሰማ ከመሆን ሌላ ድርጊቱን እንኳን ለመኮነን አልደፈሩም፡፡ አደባባይ ወጥተው መኮነን ቀርቶ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ አንድ መስመር አላሰፈሩም፡፡

ከዓለም አቀፍ መስፈርት አንጻር ደረጃቸውን ያልጠበቁና ደካማ የጤና አገልግሎት ባሉባት ኢትዮጵያ በእብሪተኛው ቡድን ለኅብረተሰቡ የጤና አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ላይ የተፈጸመው ዘረፋ፣ ውድመትና ጉዳት በ‹‹የኤስ ኤስ ኤ››ው መረጃ ላይ አለመታየቱም ቡድኑን አሳልፎ ላለመስጠት የሚደረግ ድጋፍ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም ይላል አዲስ ዘመን፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe