በዓይን ማዝ (ትራኮማ- trachoma) ህመም ምክንያት የዓይን ቆብ ሽፋሽፍት (ጠጉር) መቀልበስ (መታጠፍ) ቀዶ ህክምና ጋር በጣምራ ፍሉኦሮሜቶሎን 0.1% ተብሎ የሚጠራዉ የጸረ-ብግነት (anti-inflammatory) የዓይን ጠብታ መድኃኒት ቢሰጥ ችግሩ ተመልሶ እንዳይከሰት (እንዳያገረሽ) መከላከል እንዳልተቻለና ሌሎች ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ መፍትሄዎች እንደሚያስፈልጉ በጥናት ተመላከተ
በኢትዮጵያ በጅማ ዞን የተካሄደ ጥናት በአገራዊና ዓለም አቀፉ የትራኮማ መከላከያ ፕሮግራሞች ይበልጥ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ መፍትሄዎች እንደሚያስፈልጉ አመለከተ። “Fluorometholone as Adjunctive Medical Therapy for TT Surgery Trial” ወይም “የFLAME” የተሰኘው ጥናት በዋና ዋና ውጤቶቹ ላይ ተመርኩዞ በሰጠዉ ምክረ-ሀሳቦች መሰረት በኢትዮጵያ “የትራኮማተስ ትሪኪያሲስ” /trachomatous trichiasis (TT)/ ወይም በትራኮማ ምክንያት የሚመጣ የዐይን ቆብ ጸጉር ወደ ውስጥ መታጠፍ/ መመለስ ችግርን ከቀዶ ሕክምና በኋላ ተጨማሪ/በተደራቢነት ፍሉኦሮሜቶሎን 0.1% ተብሎ የሚጠራዉ የዓይን መድኃኒት ችግሩ ተመልሶ እንዳይከሰት (እንዳያገረሽ) መከላከል እንዳልቻለ እና መድሀኒቱም ወጪ ቆጣቢ እንዳልሆነ አሳይቷል ።
“የትራኮማተስ ትሪኪያሲስ” /trachomatous trichiasis (TT)/ ወይም በትራኮማ ምክንያት የሚመጣ የዐይን ጸጉር ወደ ውስጥ መታጠፍ/መመለስ በትራኮማ በሽታ በተደጋጋሚ ምርቃዜ (infection) ሲከሰት የሚያስከትለው የከፋ ችግር ነዉ። ሽፋሽፍቶች ወደ ውስጥ ሲቀለበሱ የአይንን የፊተኛ ክፍል፣ ብሌንን ጨምሮ፣ በመፈግፈግ መቁሰልን ቀጥሎም የብሌን ጠባሳ ያስከትላል። ይህ ችግር የእይታ መቀነስብሎም እስከ ሙሉ ዓይነ ስውርነት ሊያደርስ የሚችልም ነዉ ። በኢትዮጵያውያን እና በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ቡድን የተከናወነውና “FLAME Trial” ተብሎ የሚጠራዉ ይህ ጥናት፣ በአሜሪካ የብሔራዊ የዓይን ኢንስቲትዩት (National Eye Institute) በብሔራዊ የጤና ኢንስቲትዩቶች (NIH) ድጋፍ በጅማ ዞን የተከናወነ ነዉ። የጥናቱ አላማም በመደበኛ የቀዶ ሕክምና ፕሮግራም ማዕቀፍ ዉስጥ ፍሉኦሮሜቶሎን 0.1% የፀረ-ብግነት (anti-inflammatory) የዓይን መድኃኒት ከቀዶ ሕክምና በኋላ ያለዉን ዉጤታማነትና የችግሩን ተመልሶ መከሰት (ማገረሸት) መቀነስ ማስቻሉን መገምገም ነበር።ይህም ከትራኮማ ጋር የተያያዘ ዓይነ ስውርነትን በመከላከል ጥረት እስካሁን ያልተፈታ ችግር ነው። በጥናቱም 2,410 ተሳታፊዎች የተካተቱ ሲሆን፣ 3,240 የዓይን ቆብ ቀዶ ሕክምናዎችም ተከናውነዋል። ይህም መደበኛ የቀዶ ሕክምና ልምምዶች ሳይቀየሩ በመካሄዱ ለነባራዊው ሁኔታ በቂ ትኩረት መደረጉን ያረጋገጠ ነበር። ጥናቱ በ12 ወራት ውስጥ 98% የዕቅዱን ዉጤታማነት አሳክቷል። ይህም በተለይ በገጠር አካባቢዎች ለተካሄዱት የሙከራ ጥናቶች እጅግ ከፍተኛ የዉጤት መጠን ነበር።
በጥናቱ ላይ አስተያየት የሰጡት ዶ/ር ወንዱ ዓለማየሁ፣ ከፍተኛ የዓይን እና የትራኮማ ሕክምና ባለሙያ እንዲሁም የFLAME ጥናት ተባባሪ መሪ ተመራማሪ ሲሆኑ ጥናቱ ከቀዶ ሕክምና በኋላ በትራኮማ ምክንያት የሚመጣ የዐይን ጸጉር ወደ ውስጥ መመለስ ተመልሶ መከሰትን (ማገርሸትን) በተመለከተ በተሳካ ሁኔታ የተካሄደ ጥናት መሆኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ወንዱ እንዳሉት፦ “ከቀዶ ሕክምና በኋላ የችግሩ መመለስ እጅግ ከባድ የጤና ችግር ነው። ይህ እስከ ዓይነ ስውርነት ሊያመራ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ ሕመምና ስቃይንም ያስከትላል፣ የተጎዱ ግለሰቦችንና የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈትናል። በተለይም የቤተሰብ መሠረቶች የሆኑትን እናቶችን/ሴቶችን በተለየ መልኩ ይጎዳል።” “ከጥናቱ ዉጤት የተገኘው ማስረጃ እንደሚሳየዉ የዓይነ ስውርነትና የእይታ እክሎችን ለሚያስከትለዉ ችግር መፍትሄ ለማመላከት ያስቻለ ትልቅ ዉጤት ያሳየ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያና ለሌሎች በተመሳሳይ ችግር ለሚጠቁ አሮችም ጠቃሚ ነው ብለዋል።” የFLAME ጥናት ዋና ዳይሬክተርና የሃርቫርድ የሕክምና ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር ዶ/ር ጆን ኬምፐን ደግሞ በበኩላቸዉ፦ “የFLAME ጥናት በተሳካ መልኩ በኢትዮጵያ ምድር መካሄዱ ሀገሪቱ በዚህ ምርምር ዘርፍ ዓለምን መምራት እንደምትችል ያሳየ ሲሆን ይህም የወደፊት የሕክምና ሂደቶችን ለማሳደግ ጠቀሚታዉ ከፍ ያለ ሲሆን እና ተሳታፊዎችንና ተመራማሪዎችንም ይጠቅማል” ብለዋል። እንዲሁም “ይህን ፕሮጀክት ለደገፈዉ ለአሜሪካ ብሔራዊ የዓይን ኢንስቲትዩት እጅግ ታላቅ ምስጋና እናቀርበለን። የFLAME ጥናት ከአሁን በኋላ የትራኮማ ፕሮግራሞችን የሚመራ ሲሆን ዓይነ ስውርነትን ለመከላከል ለሚፈልጉ ሺዎች ነፃ ቀዶ ሕክምና ሰጥቷል” ሲሉ ገልጸዋል። ትራኮማ በዓለም ዙሪያ ከሚከሰቱ የተላላፊ ህመሞችመካከል ለዓይነ ስውርነት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኢትዮጵያም በዓለም ከፍተኛውን የትራኮማ ጫና ካለባቸዉ ሀገራት ትመደባለች።
ትራኮማን ከመቆጣጠር አንፃር፣ በማስረጃ የተመሠረቱ የፖሊሲ ውሳኔዎች ለአገራዊ ዕቅድና ሀብት ምደባም እጅግ አስፈላጊ ናቸው። ዋና ዋና ውጤቶች የFLAME ጥናት የፀረ-ብግንት የዓይን መድኃኒቶች ብቻ የ“ትራኮማተስ ትሪኪያሲስ” /trachomatous trichiasis (TT)/ ወይም በትራኮማ ምክንያት የሚመጣ የዐይን ቆብ ጸጉር ወደ ውስጥ መመለስ/መታጠፍ ችግር ተመልሶ መከሰትን (ግርሻን) ለመከላከል መፍትሄ እንዳልሆነ አሳይቷል። ጥናቱ በተጨማሪም ከዉጤታማ መድኃኒት በተጨማሪ የቀዶ ሕክምና ጥራት ማሻሻልም ከፍተኛ ጠቀሚታና ተፅዕኖ እንዳለው አመለክቷል። ጥናቱ የተሻለ ውጤት የሚያስገኙ፣ በማስረጃ የተደገፉ አማራጮችን መለየትን እና በውጤቶቹም መሠረት የቀዶ ሕክምና ስኬትን የሚያሻሽሉ ግብዓቶች ጥቅም ላይ አንዲውሉ ይመክራል። የተለዩ ውጤቶች
• ፍሉኦሮሜቶሎን የዓይን መድኃኒት ለአጭር ጊዜ መጠቀም የሚቻል ቢሆንም፣ ከቀዶ ሕክምና በኋላ ትሪኪያሲስን ለመከላከል እንደማይችል እና ለመደበኛ የTT ቀዶ ሕክምና ፕሮግራሞች ወጪ ቆጣቢም እንዳልሆነ አሳይቷል
• በጥናቱ ከ99% በላይ የ12 ወራት ክትትልና ከፍተኛ የተሳታፊዎች እርካታ መጠን፣ እንደዚህ ያሉ የTT ቀዶ ሕክምና ፕሮግራሞች እጅግ ከፍተኛ ዉጤት እንዳላቸው ያሳያል
• የPosterior Lamellar Tarsal Rotation (PLTR) የዓይን የቀዶ ሕክምና ስልት — በተለይ ለአዳዲስ ሐኪሞች ስልጠና እንዲሰጥና የPLTR የቀዶ ሕክምና የትግበራ አቅም እንዲሰፋ ምክረ-ሀሳብ ሰጥቷል። ምክረ-ሀሳቦች
- ፍሉኦሮሜቶሎን 0.1% ተብሎ የሚጠራዉ የፀረ-ብግነት የዓይን መድኃኒት በኢትዮጵያ “የትራኮማተስ ትሪኪያሲስ” /trachomatous trichiasis (TT)/ ወይም በትራኮማ ምክንያት የሚመጣ የዐይን ቆብ ጸጉር ወደ ውስጥ መመለስ ከቀዶ ህክምና ብሁዋላ አንደገና ተመልሶ እንዳይከሰት (እንዳያገረሽ) መከላከል እንዳልቻለ እና መድሀኒቱም ወጪ ቆጣቢ እንዳልሆነ አሳይቷል ። በመሆኑም መድሃኒቱን ለመደበኛ “የትራኮማተስ ትሪኪያሲስ” /trachomatous trichiasis ” TT ቀዶ ሕክምና ፕሮግራሞች አይመከርም።
- የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴርና አጋሮቹ በቀዶ ሕክምና ጥራት ማሻሻል፣ የ PLTR (Posterior Lamellar Tarsal Rotation) የሚባልወን የቀዶህክምና ኦዪነት ማስፋፋት እና በተቋማዊ ማሻሻያ ስልጠና ስርዓቶችን ማቋቋም ላይ እንዲያተኩሩ ጥናቱ ምክረ-ሀሳብ ሰጥቷል።። ስለ ብርሃን የህዝብ ጤናና ዓይን እንክብካቤ አማካሪ ብርሃን የህዝብ ጤናና ዓይን እንክብካቤ አማካሪ ከአገራዊና ዓለም አቀፍ አጋሮቹ ጋር በመተባበር፣ በማስረጃ የተመሠረተ ምርምርን በመደገፍ የአገር ፖሊሲን የሚመራና የረጅም ጊዜ ውጤቶችን የሚያሻሽል ሥራ ቀጥሏል።
የጥናቱ ተባባሪዎችና አጋሮች
የFLAME ጥናት በጠንካራ አገራዊና ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ ትብብር የተሳካ ነዉ። አገራዊ አጋሮች • ብርሃን የህብረተሰብ ጤናና ዓይን እንክብካቤ አማካሪ • ፍሬድ ሆሎውስ ፋውንዴሽን – ኢትዮጵያ /Fred Hollows Foundation–Ethiopia/ • የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮና የጅማ ዞን ጤና ጽ/ቤት ዓለም አቀፍ አጋሮች • Mass Eye and Ear (የMass General Brigham) / Harvard Medical School, Boston, USA • University of Pennsylvania, Perelman School of Medicine, Philadelphia, USA • Fred Hollows Foundation Melbourne, Australia • London School of Hygiene & Tropical Medicine, London, England ####################################################################### ለበለጠ መረጃ: – Dr. Aida Abashawl, Co-Principal investigator (PI), Berhan Public Health & Eye Care Consultancy, FLAME Field Coordinating Center +251911227174 aabashawl@gmail.com – Ms. Ahlam Awad Mohammed, amohammed9@meei.harvard.edu – Program Manager, Mass Eye and Ear / Berhan Public Health & Eye Care Consultancy

