በየመን ለረመዳን እርዳታ ሲታደል በተፈጠረ መጨናነቅ 78 ሰዎች ሞቱ!

በየመን ዋና ከተማ ሰንአ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የረመዳን ወርን በማስመልከት ሲደረግ የነበረ ድጋፍን ተከትሎ በተፈጠረ ትርምስ ቢያንስ 78 ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናት ገልጸዋል።በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚዘዋወሩ ቪዲዮዎች በከተማዋ ባብ አል የማን በተባለ ቦታ የነበረውን ግርግር አሳይተዋል።

በስፍራው በነፍስ ወከፍ ሲታደል የነበረውን 9 ዶላር ወይም 485 ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመቀበል በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨናነቀ ሁኔታ በትምህርት ቤት ውስጥ ተሰባስበው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ ከተማዋ በሁቲ አማጽያን ቁጥጥር ስር ወድቃለች።

እርዳታውን ሲያድሉ የነበሩ ሰዎች ታስረው ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ገልጿል።የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ እርዳታውን ከአከባቢው አስተዳደር ጋር ሳይቀናጁ በዘፈቀደ ለማደል መሞከሩ የችግሩ ምንጭ ናቸው ሲሉ ወቅሰዋል።በአደጋው በከርካታ ሰዎችም እንደተጎዱና 13 ሰዎች ደግሞ ለህይወት በሚያሰጋ ሁኔታ እንደሚገኙ በሰንአ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ገልጸዋል።

[BBC]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe