በዩኤስኤድ ስራ ማቆም ችግር ውስጥ መግባቱን ሜሪጆይ ኢትዮጽያ ገለጸ

የአሜሪካው USAID የእርዳታ ድርጅት ስራ ማቆም ከ100 በላይ ሰራተኞችን ከስራ እንዲያሰናበት ምክኒያት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ፕሮጀክቶች እንዲታጠፉ አደርጓል ብሏል፡፡ ሚሪጆይ ኢትዮጽያ ከ31 ዓመት በፊት የተቋቋመ አገር በቀል ግብረ ሰናይ የልማት ድርጅት ነው፡፡

ድርጅቱ መጋቢት 28 15ሺ ሰው ይሳተፍበታል የተባለ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ማዘጋጀቱንም ይፋ አድርጓል፡፡

ሜሪጆይ ኢትዮጽያ አረጋዊያንን እመግባለሁ ጤንነቴን እጠብቃለሁ በሚል መሪ ቃል መጋቢት 28/2017 ከ12ሺ እስከ 15ሺ ሰዎች የሚሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ነው ያዘጋጀው፡፡ ለውድድሩ የሚሆኑ ቲሸርቶች በዳሽን ባንክ እና በቴሌ ብር ይሸጣል የተባለ ሲሆን በተጨማሪም መገናኛ፡ አስኮ፡ ገዳም ሰፈር በሚገኘው በተቋሙ ማዕከላት ይሸጣል ተብሏል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe