በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላይ የግድያ ሙከራ ተቃጣ

በጥቃቱ አምስት የአካባቢው ነዋሪዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸውን አይን አማኖች ለዶቼ ቬለ DW ተናግረዋል፡፡የምክር ቤት አባላቱ የግድያ ሙከራው የተቃጣባቸው በልዩ ወረዳው በኮሬ ብሄር አባላት ላይ ይፈጸማል የተባለውን የዘር ተኮር ጥቃት ለማጣራት ወደ ልዩ ወረዳው ባመሩበት ወቅት ነበር ፡የግድያ ሙከራው በተደረገበት የዶርባዴ ቀበሌ ነዋሪ ነኝ ያሉ አንድ አይን አማኝ ጥቃቱ ትናንት ከቀትር በኋላ የተፈጸመው በቀበሌው መልካ ኦዳ በተባለ መንደር ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከፌዴራሉ መንግሥት የተላከው አጣሪ ኮሚቴ የጥቃቱ ሰለባዎችን ለማነጋገር ወደ መንደሩ ለመግባት በተቃረበበት ወቅት ነዋሪው ተሰብስቦ ሲጠባበቅ እንደነበር የጠቀሱት አይን አማኙ «በመሀል ግን የኮሚቴው አባላት ወደ መንድሩ ሊደርሱ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች እንደቀሯቸው ከኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን አቅጣጫ የመጡ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ከፈቱ፡፡ የኮሚቴው አባላቱ ወደ ኋላ የተመለሱ ሲሆን ተሰብስበው ከነበሩት ነዋሪዎች መካከል አምስት ሰዎች በጥይት ተመተው ወዲያውኑ ሞተዋል፡፡በጥቃቱ የቆሰሉ ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ወደ ጤና ተቋማት ተወስደዋል» ብለዋል፡፡በተወካዮች ምክር ቤት የአማሮ ልዩ ወረዳ ተመራጭ የሆኑት ዶክተር አወቀ ሀምዛዬ ኮሚቴው በታጣቂ ቡድኑ በገጠመው ችግር ለጊዜው የማጣራት ሥራውን አቋርጦ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ እንደሚገኝ ለቬለ DW አረጋግጠዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe