በደቡብ ወሎ ዞን፤ በደላንታ ወረዳ የመአድን ቁፋሮዉ ዳግም መጀመሩ ተነገረ

በደላንታ ወረዳ አለኋት ቀበሌ ” ቆቅ ውሀ ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ የነበሩ ሰዎች ዋሻ ተደርምሶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

የሰዎቹን ህይወት ለማዳን ሲደረግ የነበረው ጥረት በመቋረጡ የተጎጂ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ ለቅሶ መቀመጣቸውም መነገሩ አይዘነጋም።

አሁን ላይ የአካባቢው ማሕበረሰብ ተስፋ በመቁረጥ እና እርሙን በማውጣት ወደ መደበኛው የኦፓል ማዕድን የማውጣት ስራ የተሰማራ መሆኑ ተሰምቷል።

የደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የማዕድን ስራዎች ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር ቡድን መሪ አቶ በሪሁን ማህብረሰቡ ተስፋ ቆርጦና እርሙን አውጥቶ ወደ መደበኛው የኦፓል ማዕድን የማውጣት ስራ ገብቷል ብለዋል።

ከተፈጠረው አደጋ ለምን መማር አልተቻለም ? አሁን ላይስ ማዕድን ለማውጣት ከበፊቱ በተለየ ጥቅም ላይ የሚውል የተሻለ መሳሪያ አለ ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ኃላፊው ፥ ” የአካባቢው ማሕበረሰብ ኑሮውን የሚያስተዳድረው የኦፓል ማዕድን በማውጣት በመሆኑ ያለ ምንም መሳሪያ ቀደም ሲል በነበረው በባህላዊ መንገድ ስራውን እያከናወነ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የአሐዱ ሬድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe