በዴንማርክ የአስትራዜኒካ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን የወሰዱ አንዳንድ ሰዎች ላይ የደም መርጋት ችግር መከሰቱን ተከትሎ ለ14 ቀናት ክትባት መስጠት መቆሟን አገሪቱ አስታውቃለች፡፡

ዴንማርክ ከደም መርጋት ችግር ጋር ተያይዞ የኮሮና ቫረስ ክትባት መስጠት ማቆሟ ተነገረ፡፡
————————–
የዴንማርክ የጤና ዳይሬክተር የሆኑት ሶረን ብሬስሮም በሰጡት መግለጫ በዴንማርክም ሆነ በሌሎች ክትባቱ በሚሰጥባቸው የአውሮፓ ሀገራ የተከሰቱ የጎንዮሽ ጉዳቶችን በደንብ እስክናጣራ እገዳው ለሁለት ሳምንት ተጥሏል ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የመድሃኒት መቆጣጠሪያ በበኩሉ የተከሰተው ክስተት ከአስትራዜኒካ ጋር የሚያገናኘው ማስረጃ የለም ሲሉ ጉዳዩን ማጣጣላቸው ተነግሯል፡፡

የአስትራዜኒካ አምራች ለሮይተርስ በፃፈው መግለጫም ክትባቱ ከመሰራጨቱ በፊት በሰዎች ላይ በደንብ ሙከራ ተደርጎል ብሏል፡፡

ሌሎች 4 ሀገራት ኢስቶኒያ፣ ሎተኒያ፣ ሉክስምበርድ እና ላቲቪያ በክትባቱ ላይ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ክትባት መስጠት አቁመዋል ሲል ኢማሳአድ አስታውቋል፡፡ የዴንማርክ የመድሃኒቶች አቅርቦት ኤጀንሲ ከሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ጋር በመሆን በመድሃኒቱ ላይ ምርመራ መጀመሩን የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe