“በድምፃዊነቴ ዘፈኑን ለውጬ አዲስ አደርገዋለሁ” ሙሉ ቀን መለሰ

የዘለዓለም እንቅልፍ እስከሚወስደኝ

ፍቅሬ የኔ እጮኛ መቼም ያንቺው ነኝ፡፡

ለረጅም ዘመናት ስፈትንሽ ኖሬ፣

ቁርጥ ሃሣቤ ሆነ እንድትሆኚ ክብሬ፡፡

ክብሬም በመሆንሽ የሕይወቴ ሕይወት፣

በይፋ ሰጠሁሽ የጣቴን ቀለበት . . .

(ግጥምና ዜማ ሰለሞን

ተሰማ፣ ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ)

ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ

ሙዚቃን በመድረክ ላይ ወጥቶ መጫወት የጀመረው 14 ዓመቱ በ1958 . ነው፡፡ መጀመሪያ የዘፈናት ዜማም ይህቺየዘላለም እንቅልፍየምትሰኘው ዘፈን ነች፡፡

1958 . በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ ተቀጥሬ ከመሥራቴ በፊት፣ በአዲስ አበባ የምሽት ክበቦች ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ሲዘፍን ቆይቷል፡፡ ውቤ በረሃ አካባቢ በነአስገደች አላምረው ዳንስ ቤት የተጀመረው ድምፃዊነት በይፋ ዘፋኝ ወደ ማስኘት የተላለፈው ፖሊስ ኦርኬስትራን ከተቀላቀለ በኋላ ነበር፡፡በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 8 ያህል ዘፈኖችን ከሃያ ባላነሱ መድረኮች በመጫወት የዝናን ደረጃ መወጣት ጀመረ፡፡

ሙሉቀን ያንጎራጎራት ሁለተኛዋ ዘፈን እምቧይ ሎሚ መስሎየምትለው የአቶ ተስፋዬ

አበበ ግጥምና ዜማ ሰትሆን . . .የሙሉቀን ልዩ ችሎታ ወጥቶ የታየባት ድርሰት እንደነበረች የሰሙት ሁሉ የሚመሰክሩለት ይሆናል፡፡

ግጥሙን እነሆ፣

እምቧይ ሎሚ መስሎ ለምን ያታልላል፣

መልኩን አሳምሮ ሰው ያጭበረብራል፡፡

ተገንዝቤዋለሁ ተፈጥሮን መርምሬ፣

ከሰውም አለበት ብስልና ጥሬ፡፡

ሰው እያሞኘ እያታለለ፣

ውሸታም መልኩን እያሳመረ፣

ሎሚ መስሎ እምቧይ ሰው አስቸገረ፡፡

ሙሉቀን በሙዚቃው ዓለም ውስጥ በቆየባቸው 20 ዓመታት ተፈጥሮ ባደለችው ተሰጥዖ እየታገዘ ሥመ ጥሩ ድምፃዊነቱን አረጋግጧል፡፡ በአራቱም መንገዶች መጫወት ይችላል ከሚባለው ከጥላሁን ገሠሠ ቀጥሎም ይጠቀሳል፡፡

በዜማ አጨዋወት አራቱ መንገዶች የሚባሉት ድምፅን በጉሮሮ በአፍንጫ

በደረትና ሣንባ ማውጣት ማለት ነው፡፡ ብዙዎቹ ዘፋኞች በአንዱ ወይንም በሁለቱ መንገድ ብቻ ያንጎራጎራሉ፡፡ ጥላሁን ገሠሠ በዚህ ገናና ስም አለው፡፡ ከሱ ቀጥሎም ሙሉቀን መለሰ ግን በሁሉም መንገዶች የመጫወት ችሎታ እንዳለው አሳይቷል፡፡ እንዲህ ዓይነት ዘፋኞች

የድምፃቸው ከፍና ዝቅ በጣም ሲጮኹም ሆነ ሲያንሾካሹኩበት እኩል የመደመጥ ምሉዕነት አለው፡፡ ዝግ ያለም ሆነ ቀጠን ያለ ሙዚቃ ሲጫወቱ የአድማጭን ጆሮ የመያዝ ተውህቦአቸው የሚደንቅ ነው፡፡ እና ሙሉቀን በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ተርታ ከሚመደቡት ከመካከለኛው ዘመን ወደረኞቹ የተሻለ አድማጭ በማፍራት ቀዳሚ የሆነውም ስለዚሁ ነው፡፡

የሙሉቀንን የድምፃዊነት ዘመን በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

/ 1958 እስከ 1964- 65 በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥና በየበዓሉ ዋዜማና በየመድረኮች ያዜመባቸው ዓመታት

/ 1964 እስከ 1967 በሸክላ እየታተሙ የሚቀርቡ ዘፈኖች ዘመን

/ 1970 ዘፈን እስካቆመበት 1978 በካሴት እያሣተመ የቆየበት . . .ይኸን ዘርዘር አድርጎ ማየት ይቻላል፡፡

/ በይፋ መዝፈኑ ከታወቀበት 1958 እስከ 60ዎቹ መጀመሪያ በፖሊስ ኦርኬስትራ እየታጀበ በመጫወት የሚታወቅባቸው እንደየዘላለም እንቅልፍእንደኧረ ወተቴ ማሬ እመጣልሻለሁ

ቅርብ ነው አገሬ፣ እስከዚያው ጠብቂኝ ናፍቶቴ ትዳሬ . . .ዓይነቶች

እንደእንዴት ነሽ ገዳዎ . . .መለስ

አርገው ጋሜ፣

አይዞህ ወንድሜ . . .

ደሞ ገለልበሚል ቀራርቶ እያደመቀ . .

እንደ

መጀመሪያ ወደሽ አሁን ከጠላሽኝ

ሰዎች እንዳይሰሙ በምስጢር ቅበሪኝ

. . .

ዓይነት ዜማዎችን ከሶል ኤኮስና ራስ ባንድ ጋር በመሆን እያቀረበ ዝናውንና ተወዳጅነቱን ከፍ እያደረገ መጣ፡፡ ባህላዊ ዜማዎችን ወደ ዘመናዊ ያጨዋወት ስልት ቀይሮ፤ የራሱን ዘመን የሙዚቃ ጉዞ መምራቱን ቀጠለበት፡፡

3ኛው/ ዘመን 1971 ጀምሮ የመጨረሻ ካሴቱን እስከ አሳተመበት 1975 . ድረስ ያለው ወቅት ነው፡፡

ሙሉቀን በካሴት ደረጃ ስድስትየዘመናዊ ዘፈን ካቆመ በኋላ ቀድሞ ካሣተማቸው፡፡ ዘፈኖች ተመርጠው በእጀባውና ቅንብሩ አበጋዝ ክብረወርቅ ተሰይሞ የመጨረሻ የታተመው ኮምፓክት ዲስክም አለ፡፡ በዚህ ስሌት ስድስት ካሴቶች እያንዳንዳቸው በአማካይ ዘጠኝ ዘፈን ቢይዙ ካሴቶች እያንዳንዳቸው በአማካይ ዘጠኝ ዘፈን ቢይዙ ሲደመሩ 54 ዘፈኖችን ተጫውቷል፡፡ የመንፈሣዊ መዝሙር አንድ ካሴት ማሳተሙን ልብ ይሏል፡፡

ስለዚህ ሙሉቀን ዘፈን ከጀመረ አንስቶ እስካቆመበት ጊዜ ድረስ በድምሩ ወደ 80 ያህል ዘፈኖችን ተጫወቷል ማለት ይቻላል፡፡

በተቻለ ዓቅም የካሴቶቹን ኅትመት በቅደም ተከተል ለማቅረብ ልሞክር፡፡

1/ “ንገሪኝ ምነውወይንም አልማዜዋያለበት ካሴት 1970 . በዳህላክ ባንድ አጃቢነት ቅንብር ዳዊት ይፍሩ

2/ “ናኑ ናኑ ነይያለበት ካሴት 1972 . ከዳህላክ ባንድ ጋር ቅንብር ዳዊት ይፍሩ

3/ “ላኪልኝ በርሞሌወይንምምነው ከረፈደያለበትን ካሴት 1973 በዳህላክ ባንድ አጃቢነት በዳዊት ይፍሩና ዴቪድ ካሣ አቀናባሪነት

4/ እነሌቦ ነይእታለም ሥሪው ቤትሽንያለበት ካሴት 1974 . በዳዊት ይፍሩ አቀናባሪነት

5/ “እኔስ እማማዬአካል ገላ የእኛ ምን አለሽ ያደገኛየሚሉት ዘፈኖች ያሉበት 1975 በሲንቲሳይዘር በሮሃ ባንድ ቅንብር ዳዊት ይፍሩ

6 / “ውሃ ወላዋይ. . . “ቁረጥልኝ ሆዴያለበት ካሴት 1975. በኢትዮ ስታር ባንድ በሙሉቀን መለሠና ሙላቱ አስታጥቄ አቀናባሪነት

7/ 6 ካሴት ውስጥ ከታተሙት ዘፈኖች ተመርጠው በአበጋዝ ክብረወርቅ የተሠራው ኮምፖክት ዲስክ

8/ አሜሪካን አገር ያሣተመው መንፈሳዊ መዝሙር

ሙሉቀን ዘፈንን በይፋ የጀመረው 14 ዓመቱ ሲሆን፣ ያቆመው ደግሞ 20 ዓመት በኋላ 34 ዓመቱ 1978.ም፡ ፡ ልደቱ 1945. ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ 51ኛ ዓመቱን እያገባደደ ነው፡፡

የተወለደው ጎጃም አዴት ሲሆን ፣ እናቱ አርፈው ለለቅሶ የመጡት አጎቱ ይዘውት አዲስ አበባ ይመለሳሉ፡፡ በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንደተናገረው ከሆነ በአጎቱ ቤት ኑሮ ምቹ አልነበረም፡፡ ለማስተማር ዓቅም ስላልነበራቸው ወደ ዘፋኝነቱ ዓለም ተቀላቀለ፡፡

ሙሉቀን መለሠ እየተባለ የሚጠራው ፤ በአጎቱ ሥም እንጂ ወላጅ አባቱ ቄስ ገበዝ ታምር ጥሩነህ ነው የሚባሉት፡፡

ዘፈን የጀመረው የእናቱ ሞት ባስከተለበት መሪር ሃዘን ተሰዶ ወደ አዲስ አበባ በመምጣቱ ነው ብያለሁ፡፡ በፖሊስ ኦርኬስትራ የዘፈናት ሦስተኛ ዜማውእናቴ ስትወልደኝምናልባትም ለራሱ የተዜመች ሳትሆን አትቀርም፡፡

እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ፣

የፊት ጉዴን ትታ እደግ ማሞ አለችኝ፡፡

ሳቅሁኝ በልጅነት አለቀስኩ አድጌ፣

የትናንቱ ለጋ ዛሬ ነፍስ አውቄ፡፡

በምጥ መጠበቧ እምዬ ስትወልደኝ፣

ማስተማሯ ኑሯል ኑሮ እንደሚጨንቀኝ፡፡

ያለም መሽ አዳሪ አላፊ ሲነጋ፣

ሳያውቀው ይሸኛል

በተኛበት አልጋ፡፡

የለም ሕይውነት ዘላለም መደሰት፣

ከሞት ተከልሎ እንዳማሩ መቅረት፡፡

ሙሉቀን ጥንታዊና ባህላዊ ዘፈኖችን በመጫወት ዝና እያገኘ ሲሄድ እንደመሐሙድፍራሽ አዳሽ ቢሉህስተብሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ . . .

. . .እስካሁን ብዙ ሠርቻለሁ፡፡ ይኸን ሥም አልሰጡኝም፡፡ ቢሰጡኝም አልከፋበትም፡፡ ባህላዊ ዜማዎችን ባዲስ መልክ የምጫወተው ዘፈን ጠፍቶ ሳይሆን

1/ ነባር ሙዚቃዎችን ለማስታወስ ነው፡፡

2/ የአሁኑ ትውልድ ሲያደምጣቸው የሚሰማውን ስሜት ለመለካት ሲሆን . . .ሞከርነው አላፈርንበትም፡፡

3/ ባህላዊውን ዜማ ስጫወት ማሻሻል አደርግበታለሁ፡፡ የኔ አቀራረብ ከጥንቱ ለየት እንዲል አደርጋለሁ፡፡ በድምፃዊነቴም ከመጀመሪያው ዘፋኝ የተለየሁ ሌላ ሰው በመሆኔ ዘፈኑንም አቀራረቤንም ለውጩ አዲስ አደርገዋለሁ . . .በዚህም ምክንያቱት ለውጥ ስለአለበት ስጫወታቸው ዘፈኖቹ ተወደዱ፣ እኔንም አስወደዱኝ፣ ይኸን አቀራረቤን አድማጩ ጠልቶት ዘፈኞቹንም ባላደመጠ ነበር . . .በዚህ ላይም እኮ አዳዲስ ዜማዎችን አዳብዬ እየሠራሁባቸው ነው .. .” ብሏል፡፡__ (አብርሃም ረታ አለሙ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe