በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደረሰ

የፍልስጤም ከፍተኛ ባለስልጣናት ከእስራኤል ጋር በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን አስታወቁ።

ባለስልጣናቱ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከሰዓታት በፊት መጀመሩን አስታውቀዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ በግብጽና ኳታር አደራዳሪነት መደረሱንም ባለስልጣናቱ ጨምረው ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ እስካሁን ከእስራኤል በኩል ማረጋገጫ ባይሰጥም የሃገሪቱ ጦር ግን በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ ያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ ማቆሙን አልጀዚራ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከዚህ ባለፈም በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል ተገድቦ የነበረው እንቅስቃሴ በመደበኛ መልኩ ጀምሯልም ነው የተባለው።

አሁን የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ያልተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን አካቷል ከመባሉ ውጭ ግን ለምን ያክል ጊዜ እንደሆነ አልታወቀም።

እስራኤል ለጋዛ ታጣቂዎች ዋነኛ የመሳሪያ ማሳለፊያ ነው ያለችውን ቦታ መዝጋቷን ተከትሎ የጋዛ ታጣቂዎች በሳምንቱ መጨረሻ ወደ እስራኤል ሮኬት ማስወንጨፋቸው የሚታወስ ነው።

ይህን ተከትሎ እስራኤል የአፀፋ እርምጃ ወስዳለች።

እስካሁን ከእስራኤል በኩል 4 ሲሞቱ 25 የጋዛ ታጣቂዎችና ፍልስጤማውያን ህይዎትም አልፏል።

ምንጭ፡ አልጀዚራን ጠቅሶ ፋና ቢሲ ዘግቦታል

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe