በጤና ተቋማት የሳይበር ጥቃቶች መጨመራቸዉ ተሰማ

አዲስ አበባ ፤ግንቦት 19 ቀን 2012፡-የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን እየናጠ ባለበት በዚህ ወቅት መንግስታት በጤና ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል እንደሚገባቸዉ ሳይበር ፒስ ኢንስቲትዩት /Cyber Peace Institute/ ዓለም አቀፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡

‘ኮሮና ቫይረስ መከሰቱን አስታኮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ጤና ተቋማት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሳይበር ጥቃት ኢላማ መሆናቸዉን “ሳይበር ፒስ ኢንስቲትዩት” ገልጿል፡፡’

ተቋሙ ያቀረበዉ ተማጽኖ በሳይበር ደህንነት ዋና ተዋንያን ፣ ምሁራንና ፖለቲከኞች መንግስታት ለዘርፉ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል በሚል የቀረበዉን ሃሳብ ደግፈዋል፡፡

Read also:‹በወረርሽኙ ምክንያት የኢኮኖሚ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል› ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  

በሁሉም የዓለማችን ማእዘናት ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮሮና ቫይረስ መከሰቱን አስታኮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ጤና ተቋማት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሳይበር ጥቃት ኢላማ መሆናቸዉን “ሳይበር ፒስ ኢንስቲትዩት” ገልጿል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በግንባር ቀደምትነት እየተሳተፉ ያሉ የህክምና ተቋማትን እና ድርጅቶች ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ በከፍተኛ ደረጃ መከሰታቸዉን ኢንስቲትዩቱ ጠቅሷል፡፡

Read also: ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ  ምክያት ከ139 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ባለይ የሚገመት…

ይህ የሳይበር ወንጀለኞች ተግባር የሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ሲሆን ወሳኝ የሆኑ ተቋማትን አቅም በማዳከም፣ አገልግሎቶችን በማስተጓጎል እና ጠቃሚ የሆኑ የቁሳቁስ እና የኢንፎርሜሽን አቅርቦት ስርጭቶችን በማዘግየት ለታማሚዎች መድረስ የሚገባዉን ህክምና በወቅቱ እንዳይደርስ ማድረጉን ተነግሯል፡፡

በሆስፒታሎች ፣ የጤና እንክብካቤ ተቋማት እና የህክምና ምርምር ኢንስቲትዩት ላይ የሚፈጸሙትን የሳይበር ጥቃቶች ለመከላከል መንግስታት “ከሲቪል ማህበረሰብ እና ከግሉ ዘርፍ” ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

የሳይበር ፒስ ኢንስቲትዩት የተማጽኖ ጥሪዉን ተቀብለዉ ፊርማቸዉ ካኖሩት ዝነኛ የፖለቲካ ሰዎች መካከል የቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት ፣ ኡራጓይ ፣ ብራዚል ፣ ላይቤሪያ ፣ ቺሊ ፣ ስዊዘርላንድ ኮንፌዴሬሽን ፣ ሜክሲኮ ፣ ኮሎምቢያ ፣ ዴንማርክ ፣ ፖላንድ እና ስሎቫኪያ የቀድሞ ፕረዝዳንቶች እንዲሁም የቀድሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማዴሌይን አልብራርት ይገኙበታል፡፡

Read aslo:ኢትዮጵያ ለኮረና ቫይረስ ፈውስ የሚሆኑ 45 ባህላዊ መድሃኒቶች ላይ ሳይንሳዊ ምርምር…

ከዚህ ባለፈ ግዙፍ የሳይበር ደህንነት እና ቴክኖሎጂ ተቋማት መሪዎች ፊርማቸዉን ያኖሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም፡ የካስፐርስኪ /Kaspersky/ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዩጂን ካስፐርስኪ ፣ የማይክሮሶፍት /Microsoft/ ፕሬዝዳንት ብራድ ስሚዝ እና የትሬንድ ማይክሮ /Trend Micro/ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢቫ ቼን ይገኙበታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe