በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመርያው የአንጎል የደም ስር ክሊፒንግ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የአንጎል የደም ስር ክሊፒንግ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ይህ ህክምና የተደረገላት ታካሚ ከአዲስ አበባ በጥቂት ርቀት ላይ የምትኖር ሲሆን ድንገት በዕለት ሥራዋ ላይ ሳለች ከፍተኝ የራስ ህመም ይሰማት እንደጀመረና ከዚያም እራስዋን ስታ መውደቋን ታሪኳ ያስረዳል።
ህክምና ተቋም እንደደረሰችም በተደረገላት ምርመራ በአንጎልዋ ውስጥ የደም ቧንቧ መፈንዳት ምክንያት የደም መፍሰስ እንደተከሰተና የፈነዳዉን የደም ቧንቧ በቅዶ ጥገና ህክምና ባስቸኳይ ካልተስተካከለ ለሞት የሚዳርጋት መሆኑን ይነገራታል።
በወቀቱ ታካሚዋ ሀክምናውን ውጭ ሀገር ወይንም የግል የህክምና ተቋም ላይ ከፍላ መታክም ስላልቻለች ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መላኳን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በኒውሮሰርጀሪ ዲፓርትመንት አስተባባሪነትና የአንጎል ደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ህክምና ከፍትኛ ልምድ ባካበቱት ዶ/ር ቶማስ ቦጋለ የሚመራ የህክምና ቡድን ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም ሶስት ስዓት ከግማሽ በወሰደ የቀዶ ጥገና የተስተካከለ የአንጎል የደም ዝውውር እንድኖራት ማድረግ ችሏል።
ይህ ህክምና ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ደረጃ በመንግስት ሆስፒታሎች ሲሰራ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። ታካሚዋ በተደረገላት ህክምና እጅጉን እንደተደሰተች ገልጻ፥ ባሁኑ ስኣት ከህመምዋ አገግማ ወደ ቤትዋ መመለስ ችላለች ሲል የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
ለሌሎች ግንዛቤ ለመፍጠር ያግዝ ዘንድ በቀዶ ጥገና ወቅት የተወሰዱ ፎቶዎችን ለማጋራት ታካሚዋ ፍቃድዋን የሰጠች ሲሆን በየቀዶ ጥገናው ላይ የተሳተፉ አባላት ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል፦
– ዶ/ር ቶማስ ቦጋለ (የአንጎል ውስጥ የደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም)
– የነርቭ ቀዶ ሕክምና ሬዝደንት ዶ/ር መሃሪ፣ ዶ/ር ፒኔል፣ ዶ/ር ዳዊት እና ዶ/ር ብዙአየሁ ፡፡
– አስክራብ ነርስ፡ ነርስ ኢብራሂም፣ ሲስተር ሶስና እና ሲስተር መንበረ
– ዶ/ር ቦንሳ (አንስቴዚዮሎጂስት)
– አንስቴዚዮሎጂ ሬዝደንት፦ ዶ/ር ማህደር፣ ዶ/ር እየሩስ እና ዶ/ር ውበት
SourceEthio FM

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe