በጦርነቱ ምክንያት በሀገሪችን ተጨማሪ 3 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ከድህነት ወለል በታች ሊገቡ እንደሚችሉ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናት አድራጊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ፖለቲከኞች በተገኙበት ለ2 ቀናት የቆየ ከፍተኛ የፖሊሲ ፎረም አካሂዷል።

በፎረሙም በ4 ዋና ጉዳዮች ላይ የትዘጋጁ ጥናቶች ለውይይት ቀርበዋል። ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጂዲፒውን በ1% ሊቀንስ እንደሚችልና 71 ሚልዮን የሚጠጋው ህዝብ ደግሞ በዋጋ ግሽበት የተነሳ ከድህነት ወለል በታች ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያም 33% የዋጋ ግሽበት ያስተናገደች ሲሆን ከዚህም ውስጥ 13% ሚሆነው በጦርነቱ ምክንያት የመጣ መሆኑ በተደረጉ ጥናቶቾ ተመላክቷል።

በሀገሪቷም ተጨማሪ 3 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ከድህነት ወለል በታች ሊገቡ እንደሚችሉና ጂዲፒያችንም ወደ 7% ሊቀንስ ይችላል ነው የተባለው።

ከ40% በላይ ከሁለቱ ሀገራት ምርቶች የምታስገባው ኢትዮጵያ ነዳጅ፣ ማዳበሪያና ምግብ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሮባታል፤ የኮሮና ወረርሽኝ፣ በሀገሪቱ የተከፈተው ጦርነት ፣ የተለያዩ ብድሮች፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና ሌሎች ምክንያቶች ግሽበቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደቻለ ተገልጿል።

ለዚህ ሁሉ ችግር ምርታማነትን ማሳደግ፣ የነዳጅ አጠቃቀማችንን ማስተካከል ቢቻል መቆጠብ፣ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ማምረት፣ የአረንጓዴ ኋይልን ማጠናከር፣ ግጭትን ማስቆምና ሌሎችም እንደ መፍትሔ ተጠቁመዋል።

የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በመስራት ለውይይት የሚያቀርበው ማኅበሩ ባለፈው ዓመት 10 ጥናቶችን ያቀረበ ሲሆን ሌሎች የምርምር ስራዎችንም እንደሚያቀርብ አስታውቆ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በጋራ እየሰራ ያለ ገለልተኛ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe