በፖርላማ ስብሰባ ላይ በማይገኙ የምክር ቤት አባላት ላይ ጠንክር ያለ እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የማይገኙ የምክር ቤት አባላት ላይ አፈገባኤው ጠንክር ያለ እርምጅ እንዲወስድ ተጠየቁ፤

በምክር ቤቱ የአሰራርና የስነ ምግባር ደንብ መሠረት ማንኛውም የምክር ቤት አባል ለስራ ጉዳይ ከሀገር ውጪ ካልሆነ በቀር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤት ተገኝተው ሪፖርት በሚያቀርቡበት ቀን እንዲሁም የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እና የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ በሚያቀርቡበት ወቅት ማንኛውም የምክር ቤት አባል የመገኘት ግዴታ እንዳለበት ደንቡ ይደነግጋል፤

ሆኖም በዛሬው እለት የ2013 በጀት ዓመት የፌደራል መስሪያ ቤቶች ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት በሚቀርብበት ወቅት አብዛኛዎቹ የምክር ቤተ አባላት አለመገኛታቸውና ወንበራቸው ባዶ ሆኖ መገኘቱን መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ ደንብ መጣሱን የገለፁ የምክር ቤቱ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ አስቀድሞ በደብዳቤ እንዲያውቁት ቢደረግም ሚኒስትሮችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ተመራጮች አለመገኛታቸውን አስታውቀዋል፤

ምክር ቤቱ የሚመራበት ደንብ ሲጣስ በዝምታ መመልከት የለበትም ያሉት አቶ ክርስቲያን ያለ ምክንያት በስብሰባ ላይ በማይገኙ  የምክር ቤት አባላት ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ጠንክር ያለ እርምጃ እንዲወስዱ አቶ ክርስቲያን ጠይቀዋል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe