ኢራን በቀጠናው የነገሰውን ውጥረት ለማርገብ ከአሜሪካ ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡ አሜሪክ ሁላችንንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ሃሳብ ይዛ ለመነጋገር ከፈቀደች ለንግግር ለመቀመጥ ኢራን ዝግጁ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ለሰላማዊ አገልግሎት መሆኑን የምትገነዘብ ከሆነና ማዕቀቧንም ለማንሳት ዝግጁ ከሆነች በቀጥታ መነጋገር ይችላል ብለዋል፡፡
ሌሎች አገራት እንደሚያደርጉት ለምን ዩራኒየም ከሌሎች አገራት አስገብቶ ለሰማዊ አገልግሎት ማዋልን ለምን ኢራን ምርጫዋ አልሆነም ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ በራሳችን አቅም ማበልጸግ እየቻልን ለምን ከሌሎች እናስገባለን ይህን ለማድረግ ፈቃደኞች አይደለንም ብለዋል፡፡
በ12ቱ ቀናት ጦርነት ውስጥም የኒውክሌር ጣቢያዎችችን እጅግ ከባድ የሚባል ጉዳት አጋጥሟቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በዝርዝር የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ያነሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መናገር የሚቻለው ከፍተኛ የሚባል ጉዳት እንደደረሰበት ብቻ ነው ለጊዜው ብለዋል፡፡
በዚህ ወቅት በደረሰው ጉዳት ምክንያት ዩራኒም እያበለጸግን ባይሆናም፤በቅርቡ ግን ይህን ማድረጋችንን እንቀጥላለን የሚያስቆመን ሃይል አይኖርም አሁን ጉዳዩ ወደብሔራዊ ኩራት የተሸጋገረ በመሆኑ በቀላሉ የሚቆም አይደለም ብለዋል፡፡
ነገር ግን ለሰማዊ ንግግር አሁንም ቅድሚያ እንሰጣለን ብለዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የኒውክሌር ፕሮግራማችንን ለማጥፋት ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሔ እንደሌለው ለመግለጽ እወዳለሁ በማለት ተናግረዋል፡፡ በርግጥ በአሁኑ ጥቃት የኒውክሌር ፕሮግራም መሠረቶቻችን እንዲወድሙብን ተደርገዋል፤ነገር ግን ይህንን መልሶ የሚጠግነው አቅም የማንም ሳይሆን የእኛ በመሆኑ ዳግም እንመልሰዋለን ብለዋል፡፡

