የኪ ሃውሲንግ 4ተኛ ዙር የቤት እድለኞች የእጣ መለያ መርሐግብር ተካሂዷል።
በ83ሺህ145 ቅድመ ክፍያ እና ከ2000 ብር በሚጀምር ወርሃዊ ቁጠባ እየተካሄደ ያለው 4ተኛ እጣ የኪ ሃውሲንግ የቤት እድለኞች መለያ መርሐግብር በዛሬው እለት ባለ እድለኞቹ በተገኙበት ተካሄዷል።
ዛሬ በተካሄደው 4ተኛ እጣ የኪ ሃውሲንግ የቤት እድለኞች መለያ መርሐግብር የ174 ቤቶች እጣ ወጥቷል።
በዛሬው የቤት እጣ አወጥጥ ውስጥ ከሶስቱም ዙር የተወጣጡ ሰዎች መካተታቸው ተገልጿል።
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን “Economies of Scale” ላይ የተመሰረተ ሞዴል ቀርዖ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰባችንን ክፍሎች የቤት ባለቤት እያደረገ እንደሚገኝ የኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ዋና ስራ አስፈሚ አቶ ግሩም ይልማ ገልጿዋል።
ወደ ገበያው ከተቀላቀለ በአንድ አመት ከስድስት ወር ውስጥ መቶዎችን በአዲስ አበባ ስድስት ሳይቶች እና በባህርዳር ከተማ የቤት ባለቤት አድርጓል ተብሏል
በአሁኑ ሰዓትም 20ሺህ የሚደርሱ አባላት እንዳለው ገልጾ ኪ መንደር የተሰኘ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል።
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን Key-CHF የተሰኘ ሞዴል ቀርፆ በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ለ100,000 ቤት ፈላጊዎች በሞዴሉ መሰረት በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ዋና ከተሞች ላይ ግንባታቸው በወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች የተጠናቀቁ ቤቶችን ከአልሚዎች ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት በመግባት በአመት ሁለት ጊዜ እድለኞችን በዕጣ በመለየት የቤት ለማድረግ እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑ ተገልጿል።

