በ6 ቀናት ለ 88 የልብ ሕሙማን ሕፃናት የልብ ሕክምና መሰጠቱ ተገለጸ

በኢትዮጲየያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ከኪንግ ሰልማንሁማኒተሪያን ኤይድ ኤንድ ሪሊፍሴንተር( KSrelief) ሲሰጥ የቆየው የህክምና ተልዕኮ በ6 ቀናት ለ 88 የልብ ሕሙማን ሕፃናት የልብ ሕክምና በመስጠት በስኬት አጠናቋል።

ለ8 ቀንናት ይቆያል ተብሎ የተጠበቀው የኪንግ ሰልማን ሁማኒተሪያን ኤይድ ኤንድ ሪሊፍ ሴንተር( KSrelief) የሕክምና ተዕልኮ ከኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ጋር በመተባበር በጥራትእና በፍትነት በመስራት በ6 ቀና ማጠናቀቅ ተችሏል።

በተልዕኮ ከኪንግ ሰልማን ሁማኒተሪያን ኤይድ ኤንድሪሊፍ ሴንተር የመጡ 30 የህክምና ባለሙያዎች ከማዕከሉ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ባከናወኑት የልብ ህክምና 88 ሕፃናት የልብ ህክምና አግኝተዋል።

የህክምና ቡድኑ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለ24 ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና እንዲሁም ለ64 ህፃናት ደግሞ በደም ስር በኩል የሚሰጥ የልብ ህክምና ወይም (cathertarazation) ህክምና የተሰጠ ሲሆን በዚህም በአስቸጋሪ ሁኔታ ለነበሩ እና ህክምናውን ለማግኘት በተስፋ ሲጠባበቁ የነበሩ ባጠቃላይ 88 ህፃናት ታክመዋል።

እ.ኤ.አ. በ2015 በሳኡዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን ቢንአብዱላዚዝ የተቋቋመው የንጉሥ ሳልማንሁማኒተሪያን ኤይድ ኤንድ ሪሊፍሴንተር የህክምና ቡድን የፈፀመው የህክምና አገልግሎት በብር ሲተመን ከ39 አስከ 51 ሚልየን ብር ነው።

ተቋሙ ከሳኡዲ አረቢያድረስ በመምጣት ላበረከተው ትልቅ ኣስተዋፅኦ ላቅ ያለ ምስጋናችን እየገለፅን አጋርነታቸውን በማስቀጠል በልብ ሕመም ከሚሰቃዩ ሕፃናት ጎን እንዲቆሙ ለዝግጅት ክፍላችን ከላከው መግለጫ ላይ ተመልክተናል።

የተሰበሩ ልቦችን በጋራ እንጠግን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe