በ64 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ምርጫ አይካሄድም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14/2013 ድምጽ መስጠት የማይቻልባቸውና ምርጫው ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ የተወሰነባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም መግለጹ የሚታወስ ነው።

ከዚህ ውስጥ ለምን ያህል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቀመጫዎች እና የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ምርጫው እንደማይካሄድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በዝርዝር አቅርቧል። በዚህም፦

• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል – ለ4 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ13 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤

• በኦሮሚያ ክልል – ለ7 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ7 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤

• በአማራ ክልል – ለ10 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ9 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤

• በደ/ብ/ብ/ህ ክልል – ለ16 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ22 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤

• በሐረሪ ክልል – ለ2 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤

• በአፋር ክልል – ለ2 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ7 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤

• ሶማሌ ክልል – ለ23 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ72 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ በሰኔ 14 ምርጫ የማይካሄድባቸው ናቸው።

በአጠቃላይ ሰኔ 14 በ64 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ምርጫ #የማይካሄድ ሲሆን በእነዚህ አከባቢዎች ምርጫው ጳጉሜ 1 የሚካሄድ ይሆናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe