በ83 አመታቸው የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት አዛውንት “ለመማር አይረፍድም” ይላሉ

አዛውንቷ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ካጠናቀቁ ከ60 አመት በኋላ ነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የተመለሱት
ከአንድ ሴሚስተር በላይ እንደማይዘልቁ ስጋት ገብቷቸው የነበረው አሜሪካዊት ምኞታቸውን አሳክተዋል

የ83 አመቷ አሜሪካዊት ከሆዋርድ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

ማሪ ፎውለር የተባሉት አዛውንት የዩኒቨርሲቲው በእድሜ የገፉ ምሩቅ ሆነዋል።

ማፕል ስፕሪንግስ የመጸሃፍ ቅዱስ ጥናት ኮሌጅ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት ፎውለር ከ60 አመት በኋላ ዳግም ወደ ትምህርት ተመልሰዋል።

“ከ1959 በኋላ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስመለስ ከአንድ ሴሚስተር በላይ የምዘልቅ አልመሰለኝም፤ ለሶስተኛ ዲግሪዬ ማሟያ ተንቀሳቅሼ መረጃ መሰብሰብ እችላለሁ የሚለውም ያስጨንቀኝ ነበር” ሲሉ ያወሳሉ አዛውንቷ።

ፎውለር ስጋታቸውን ሁሉ እየጣሉ ለሶስት አመት በሃይማኖት ጉዳይ ያተኮረ ትምህርታቸውን ተከታትለውና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ማሟያ በብቃት አቅርበው በቅርቡ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

በምረቃቸው ወቅትም ከኤቢሲ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ “ለመማርና ምኞታችን ለማሳካት እድሜ ገደብ እንደማይሆን ከእኔ በላይ ማሳያ የለም” ብለዋል።

አዛውንቷ አሜሪካዊት በ80 አመታቸው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ያነሳሳቸው ወላጆቻቸው ለትምህርት የነበራቸው አመለካከት እንደሆነ ያወሳሉ።

“እናት እና አባቴ ማንበብና መጻፍ ለመቻል መማር በተከለከለበት ዘመን ነው የተወለዱት፤ አባታችን እኛ ነን ማንበብና በእስኪርቢቶ መፈረም ያስተማርነው” በሚልም ወላጆቻቸው ለትምህርት ከፍተኛ ቦታ ይሰጡ እንደነበር አስታውሰዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ሆዋርድ ዩኒቨርሲቲ በ156 አመት ታሪኬ በእድሜ የገፉ ምሩቅ ናቸው ላላቸው የ83 አመቷ ማሪ ፎውለር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክቱን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe