ቡርኪናፋሶ እና ማሊ በአሜሪካ ዜጎች ላይ የቪዛ እገዳ ጣሉ

ሁለቱ የሳህል ቀጣና ሃገራት በትራምፕ አሰተዳደር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው በኋላ ተመሳሳይ እርምጃ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ወስደዋል።

የቡርኪናፋሶ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቡርኪናፋሶ ተመሳሳይ የቪዛ ውሳኔን በአሜሪካ ዜጎች ላይ ጥላለች ሲል የማሊ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም በአሜሪካ የተጣለውን ተመሳሳይ የቪዛ እርምጃ በአሜሪካ ዜጎች ላይ መጣሉን ገልጿል።

ዶናልድ ትራምፕ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የጉዞ እገዳ በ39 ሃገራት ላይ መጣላቸው ሲታወስ የሃገራቱ ዜጎች በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ መግባትም አይችሉም።

የቡርኪናፋሶ እና የማሊ ውሳኔም አሜሪካ እንዳደረገችው ሁሉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ሃገራቸው እንዳይገቡ ይከለክላል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ደቡብ ሱዳንና ሶሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ የጉዞ እገዳ መጣላቸው ይታወሳል።

በተጨማሪ በሌሎች 15 ሃገራት ላይ በከፊል እገዳውን ጥለዋል።ከነዚህ ሃገራት መካከል አሜሪካ አስተናጋጅ በሆነችበት በ2026 የአለም ዋንጫ አፍሪካን በመወከል የሚሳተፉት ሴኔጋልና አይቮሪኮስት ይገኙበታል።

በትራምፕ አስተዳደር ወደ  አሜሪካ ሙሉ ለሙሉ እንዳይገቡ የተከለከሉት እነማን ናቸው?

-ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ አፍጋኒስታን፣ ቡርኪናፋሶ፣ በርማ፣ ቻድ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሃይቲ፣ ኢራን፣ ላኦስ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ሴራሊዮን፣ ሶሪያ፣ የመንና በፍልስጤም በሚሰጥ የጉዞ ሰነድ የሚጓዙ ግለሰቦች።

በከፊል እገዳው የተጣለባቸው ሃገራት

– ናይጄሪያ፣ አንጎላ፣ አንቲጉያና ባርቡዳ፣ ቤኒን፣ ቡሩንዲ፣ አይቮሪኮስት፣ ኩባ፣ ዶሚኒካ፤ ጋቦን፣ ጋምቢና፣ ማላዊ፣ ሞሪታኒያ፣ ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ፣ ቶጎ፣ ቬኔዙዌላ፣ ዛምቢያና ዚምባቡዌ ናቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe