የጤና መረጃ ቡናን ተዓምረኛው(miracle) መጠጥ ይሉታል በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች፡፡ ይህን እንዲሉ ያስቻላቸው ዋነኛው ምክንያት፣ ቡናን መጠጣት ለጤና የሚሰጣቸውን በርከቶች በመገንዘባቸው ነው፡፡
ብዙ ሰዎች በዕየለቱ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በተነቃቃና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመከወን እንዲችሉ ቡናን በጥዋት እንደሚጠጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ከ20 አመታት በላይ በቡና ውስጥ በሚገኘው ‹‹ካፌይን›› በተባለው ንጥረ ነገር ዙሪያ ጥናት ሲያደርግ የቆየው ኮርኔሊስ የተባለው ተመራማሪ እንደገለጸው፣ለበርካታ አመታት ቡና ጤናማ ያልሆነ መጠጥ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፤ነገር ግን ቡናን መጠጣት ከጉዳቱ ይልቅ በርካታ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ማረጋገጡን ገልጿል፡፡
በመሆኑም ቡናን በአግባቡ መጠጣት ከሚያስገኛቸው የጤና ጥቅሞች መካከል፡-
👉ዓይነት 2 የተባለውን የስኳር በሽታ ይከላከላል፣
👉ከፓርኪንሰን በሽታ ይከላከላል፣
👉ለመርሳት በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል፣
👉ሰዎች ረጅም ዕድሜ እንዲኖራቸው ያግዛል፣
👉ለድብርት የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል፣
👉በጉበት ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል፣
👉ለአንጀት ፤ ለጡት እና ለታይሮይድ ካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሰል፡፡
ቡና መጠጣት የሚያስከትላቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች፡-
ቡናን መጠጣት ከላይ የተዘረዘሩትን የጤና ጥቅሞች የማስገኘቱን ያክል አንዳንዴ ደግሞ በጤና ላይ የሚያስከትላቸው የጎንኞሽ ጉዳቶችን ሊኖሩ እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ያስገነዝባሉ፡፡
ለአብነትም፡-
👉የልብ ምትን ይጨምራል፣
👉እንቅልፍ ማጣት ሊያስከትል ይችላል፣
👉የፕሮስቴት እጢ ባለባቸው አረጋውያን ዘንድ የሽንት መጠንን ሊጨምር ይችላል፣
👉ለአጥንት ጤና ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ማለትም እንደ ካልሲየም እና ብረት ያሉ ቁልፍ ማዕድናትን የመምጠጥ አቅምን ሊቀንስ ይችላል፡፡
👉ነፍሰጡር ሴቶች ቡና አብዝተው የሚጠጡ ከሆነ የፅንስ መቋረጥ(መጨንገፍ) ሊያስከትልባቸው ይችላል፡፡
ስለዚህ ቡናን በአግባቡ በመጠቀም ለጤና የሚያስገኛቸውን በረከቶች ማግኘትና ከጎንዮሽ ጉዳቶች ደግሞ ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ከዩፒአይ(UPI) ያገኘነው የጤና መረጃ ያመለክታል፡፡

