ቡና ባንክ ለ7ኛው ዙር  ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር አሸናፊ የቤት አውቶሞቢል ሸለመ

  • / ሄለን በቀለ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ስትሆን ሌሎች አሸናፊዎችም ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡

ቡና ባንክ አክሲዮን ማኅበር ለሶስት ወራት ሲያካሂድ የቆየውን ሰባተኛውን ዙር በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ደንበኞች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃግብር ማጠናቀቂያ ምክንያት በማድረግ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ለዕድለኛ ደንበኞቹ አስረከበ፡፡

በባንኩ ዋና መ/ቤት በተካሄደው በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ አሸናፊ ለሆኑት ባለዕድለኞች፥ የአውቶሞቢል፣ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ፣ የሪፍሪጅሬተሮች፣ የዘመናዊ ስልኮች ፣ የፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች እና የውሃ ማጣሪያ ሽልማቶችን አበርክቷል።

ቡና ባንክ  የጎላ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ በማተኮር ባዘጋጀው በዚህ የቁጠባ እና ሽልማት ፕሮግራም ዜጎች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የቁጠባ ባህልን ከማሳደግ በተጓዳኝ የትራንስፖርት ዘርፍ ተዋንያንን በልዩ ሁኔታ በማበረታታት ገንዘባቸውን ቆጥበው ተሸላሚ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን መርሃ ግብር በማዘጋጀት በትራንስፖርት ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞቹ አጋር ሆኖ የቆመ ባንክ  ነው፡፡

የሽልማት መርሃ-ግብሩ በማንኛውም ቀላልና ከባድ የፈሳሽ እና ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ፣ መደበኛ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ‘ሚኒባሶች’፣ ‘ሚድ ባሶች’፣ ‘ሜትር ታክሲዎች’፣ ‘ባለሶስት እግር ታክሲዎች’ እንዲሁም የመካከለኛ እና ከፍተኛ ሃገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች  ላይ የተሰማሩ ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች ረዳቶች እና ትኬት ቆራጮችን ጨምሮ  በዘርፉ ውስጥ የሚሰሩ ደንበኞች በዚህ የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር ተሳታፊ  ሆነዋል።

bunna bank

ባንኩ በዛሬው የሽልማት መርሃ ግብር ለአንደኛ ዕጣ ዘመናዊ ሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢል፣ ለሁለተኛ ዕጣ አንድ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ፣ ሶስተኛ ዕጣ አራት ፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች፣ አራተኛ ዕጣ አራት ሪፍሬጅሬተሮች፣ አምስተኛ ዕጣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ስድስተኛ ዕጣ አራት የውሃ ማጣሪያዎች፣ እና ሰባተኛ ዕጣ አስር ዘመናዊ ሞባይል ቀፎዎችን ለባለዕድለኞች በዛሬው ዕለት አስረክቧል።

የገንዘብ ቁጠባ የግለሰቦችን ኑሮ ከመለወጥ ባለፈ ለምጣኔ-ሐብት ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን ህብረተሰቡ የዳበረ የቁጠባ ባህል እንዲያሳድግ ለማድረግ ቡና ባንክ የበኩሉን ሚና በመጫወት በየጊዜው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ የቁጠባ ፕሮዳክቶችን በመቅረጽና ማበረታቻ ሽልማቶችን በማዘጋጀት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የማህበረሰብ ክፍል የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጓል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ  የቁጠባ ባህል በአገር-አቀፍ ደረጃ እንዲያድግ ለማገዝ ልዩ ልዩ መርሃግብሮችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው ቡና ባንክ በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የህብረተሰብ  ክፍሎች ያዘጋጀውን 7ኛ ዙር የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር በማጠናቀቅ የሎተሪ ዕጣዎቹን መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በህዝብ ፊት በይፋ ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡

በሌላ በኩል የ11ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ መርሃ ግብር በሂደት ላይ ሲሆን በቅርቡ ሲጠናቀቅ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በሚከናወን ይፋዊ ዕጣ የማውጣት ስነ-ስርዓት አሸናፊዎቹ የሚለዩ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም 8ኛው ዙር በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ደንበኞች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብርም በቅርቡ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡

ቡና ባንክ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ ከተመሰረተ 13 ዓመታትን ያስቆጠረውና ከ14ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ሲሆን በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ በከፈታቸው 464 በላይ ቅርንጫፍ ባንኮቹ አማካኝነት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ በባንክ ዘርፍ ላይ የሚሰራ ኩባንያ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe