ቡና ባንክ በቁጠባ መርሀ ግብር ተሸላሚ የሆኑ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎችን ይፋ አደረገ

የቡና ባንክ ደጃች ውቤ ቅርንጫፍ ደንበኛ በእጣ ቁጥር 4909927 የ2021 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና አሸናፊ ሆነዋል ።
ቡና ባንክ ለመምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ለ2ኛ ጊዜ ያዘጋጀውን እና ላለፉት ወራት ሲያካሒድ የቆየውን ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሐ ግብር አጠናቆ አሸናፊዎችን ዛሬ ሰኔ 9 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተከናወነው የእጣ ማውጣት ስነስርአት ይፋ አድረጓል ።
ሽልማቶቹ አንደኛ እጣ የ2021 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና ፤ 12 ላፕቶፖች ፤ 12 ታብሌቶች ፤ 24 ስማርት ስልኮች እና 6 የጉብኝት ጥቅሎች ናቸው።
ባንኩ የሀገር ባለውለታ ናቸው ያላቸው የሁለቱም ዘርፎች ባለሙያዎችን ለማበረታታትና የቁጠባ ባህል ለማዳበር ሲባል በሁሉም ደረጃ ያሉ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ተገልጿል ።
መርሀ ግብሩ 55 መምህራንና የጤና ባለሙያዎችን በአምስት የሽልማት ዘርፎች ከመኪና ጀምሮ ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የሽርሽር ጉዞን ያካተተ ነው ተብሏል ።
ቡና ባንክ ከ12 አመታት በፊት የተቋቋመ ሲሆን 339 ቅርንጫፎች አሉት። ከ13 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ቡና ባንክ የደንበኞቹ ቁጥር ከ1.9 በላይ ማድረስ መቻሉን አስታውቋል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe