ቡና ባንክ አዲስ መለያ ምልክት (ሎጎ ) መቀየሩን አስታወቀ

አዲሱ አርማው ራእይና ተልእኮውን እንዲወክል ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ

ከተመሰረተ 12 ዓመታን ያስቆጠረውና ግዙፍ ካፒታልና ከ14ሺ በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት  ቡና ባንክ ከምስረታው ጀምሮ  ሲጠቀምበት የነበረውን መለያ ምልክት (ሎጎ) መቀየሩን  አስታወቀ።

ቡና ባንክ በአዲስ የመለያ  ምልክት አርማ እና ቀለም ለመምጣት ለኹለት ዓመታት ያህል የጥናት እና የዝግጅት ሥራዎችን አከናውኖ በመጨረሻም አዲሱን የንግድ ምልክት አርማና ቀለም በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

የቡና ባንክ ቺፍ ስትራቴጂክ ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ አዲሱን አርማ በማስመልከት የተዘጋጀውን ኬክ በመቁረስ አርማውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ይህ ባንኩ ተቀየረው አዲሱ አርማና ቀለም በኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት   ባለስልጣን ተመዝግቦ የፀደቀ ሲሆን፤ አዲሱ አርማ እና ቀለም የባንኩን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች እንዲወክል ሆኖ የተዘጋጀ መሆኑን የቡና ባንክ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አባይነህ ሃብቴ በዛሬው ዕለት በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ  ገልፀዋል።

Bunna Bank
Bunna Bank

ባንኩ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረው የመለያ ምልክት በቀላሉ ለመታወስ አስቸጋሪና ለመረዳትም ውስብስብ መሆኑን ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት በማረጋገጡ፤ ለአጠቃቀም ቀላል፣ ለመረዳት ግልፅ የሆነና በቀላሉ መታወስ የሚችል የመለያ አርማ እና ቀለም እንዲዘጋጅ መወሰኑን አባይነህ ተናግረዋል።

አዲሱን የባንኩን የንግድ መለያ ምልክት እና ቀለም ለመቀየር በጨረታ ከተወዳደሩ የብራንዲንግ ኩባንያዎች ውስጥ አሸናፊ የሆነው “ቤሪ አድቨርታይዚንግ” የመለያ ምልክቱን ለውጡን ሥራ ያከናወነ ሲሆን፤ ኩባንያው የንግድ መለያ ምልክት እና የቀለም ዝግጅቱን ከብራንድ መመሪያ ሰነዱ ጋር አጠናቆ ለባንኩ አስረክቧል።

Bunna Bank
Bunna Bank

አዲሱ የንግድ መለያ ምልክት ከሶስት ምስሎች የተዋቀረ ሲሆን፤ እነርሱም የአይን፣ የአድማስ እና ክብ ቅርፅን የያዙ ምስሎች ናቸው።

በዚህም የመንቃትን፣ የአዲስ ቀን ጅማሮን እንዲሁም ብዙ ሆነን እንደ አንድ የምንሰባሰብበት ትርጉምን እንዲወክሉ ተደርገው መቀረፃቸውን የቤሪ አድቨርታይዚንግ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መላኩ ባህሩ  ገልፀዋል።

ቀለማቱ የአላማ ጥንካሬ፣ ጥልቅ የማገልገል ፍላጎት፣ የሥራ መነሳሳትን እንዲሁም የምንጊዜን ታማኝነትን፣ ለዓላማ ቁርጠኝነትን እና በዕውቀት መስራትን ይወክላል ተብሏል።

ቡና የኢትዮጲያ መለያ ከመሆኑም በላይ ያለው ማህበራዊ እሴትም ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት የባንኩ የኮሚዩኒኬሽን እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ብርሀኑ ናቸው፡፡ አቶ መላኩ እንደገለጹት ባንኩ በአሁኑ ሰአት 1.8 ሚሊዮን ደንበኞች ፤ 14 ሺህ ባለአክሲዮኖች እና 2700 ሰራተኞች አሉት ብለዋል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe