ቡና ባንክ እና ሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ (Rays MFI) በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

ቡና ባንክና ሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ በተለያዩ የፋይናንስ ዘርፎች በትብብር ለመሰራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በቡና ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው የፊርማ ስነስርዓት ላይ እንደተገለጸው ስምምነቱ በሁለቱ የፋይናንስ ተቋማት መካከል የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽነት የማስፋት፣ የዲጂታል ክፍያዎችን የማሳለጥ፣ እንዲሁም የኔትወርክ እና የሀብት ማሰባሰብ ትስስርን በመፍጠር የገንዘብ አቅርቦትን ለማሳደግ ያግዛል ተብሏል። የሁለቱ ተቋማት ስምምነት በተለይም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ የሚያሳድግና ሚያስተዋዉቅ እንደሚሆንም ተስፋ ተጥሎበታል።

በስምምነቱ መሰረት በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በሶማሌ ክልል የሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ እና የሰሃይ ፔይ (Sahay Pay) ቅርንጫፎች እና ወኪሎችን በመጠቀም ከቡና ባንክ ወደ ሬይስ እና ሰሃይ አካውንቶች የገንዘብ ዝዉዉሮችን ማድረግ የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል።

ስምምነቱን ከቡና ባንክ አቶ ለውጤ ጥሩሰው የባንኩ ቺፍ ባንኪንግ ሰርቪስ ኦፊሰር እና ከሬይስ ማይክሮ ፋይናንስ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዲዓዚዝ ሀሰን ተቋማቸውን ወክለው ተፈራርመዋል፡፡

የጋራ ስምምነቱ የሁለቱን ተቋማት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክርና ለደንበኞቻቸው ቀልጣፋ አገልግሎትን በዘመናዊ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ከመሆኑ ባሻገር በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በተለይ በሶማሌ ክልል የቡና ባንክን የስራ እንቅስቃሴ በማስፋት ገፅታውን የሚገነባና የሚያሳደግ ይሆናል ተብሏል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe