ቡና ባንክ የሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢል መኪና አሸናፊን ይፋ አደረገ

ቡና ባንክ የ3ተኛ ዙር የመምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር ተሸላሚዎችን ይፋ አደረገ።

በዛሬው እለት በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተካሄደው የዕጣ ማውጣት ስነስርአት ከደሴ ዲስትሪክት፣ የሙጋድ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑት ወ/ሮ ፋንታዬ ደምሌ ሞላ በሎተሪ ቁጥር 8074368 ሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢል መኪና አሸናፊ ሆነዋል፡፡

2ኛ ዕጣ ቁጥሮች 9614144 ከ ሀሙሲት ቅርንጫፍ፣ ባህርዳር ዲስትሪክት እና 0696785 ከ ብስራት ገብርኤል ቅርንጫፍ የላፕቶፕ አሸናፊዎች ሁነዋል።

3ኛ ዕጣ 2 ታብሌቶች የወጡ ሲሆን የዕጣ ቁጥር 3467580 ከ ዘምባባ ቅርንጫፍ፣ ባህርዳር ዲስትሪክት እና

4843092 ከ የጁቤ ቅርንጫፍ፣ ደብረማርቆስ ዙሪያ አካባቢ አሸናፊ ሆነዋል

 

የትምህርትና ጤና ባለሙያዎችን ተሸላሚ የሚያደርገው 3ኛው ዙር የቡና ባንክ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃግብር አሸናፊዎች መለያ ዕጣ ሐምሌ 20 ቀን 2015 .ም በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በይፋ ሲወጣ መርሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቡን ባንክ ኮሚዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን የኮርፖሬት ዲቪዥን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ብርሃኑ የተለያዩ የይቆጠቡ ይሸለሙ መርሃ ግብሮችንና አገልግሎቶችን መቅረዕና ወደ ደንበኞች ማድረስና ማበረታታት ቡና ባንክ የኢትዮጵያን ልማት ከሚደግፍባቸው መንገዶች መሀከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው የዚህ አይነት መርሃ ግብሮች ሌሎች ደንበኞችም በባንኩ ቁጠባ እንዲጀምሩ በማድረግ የመምህራን እና የጤና ባለሙያዎችን አርአያነት ያለው ተግባር እንዲደግፉ ያነሳሳል ብዬ አምናለሁ ብለዋል፡፡ መርሃ ግብሩ ከየካቲት 15 ቀን 2015 .ም እስከ ሰኔ 20 ቀን 2015 .ም ድረስ ለአራት ወራት ሲካሄድ ቆይቷል።

በትምህርትና በጤና ዘርፍ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች በተዘጋጀው በዚህ የቁጠባና ሽልማት መርሃግብር ተሳታፊ ለነበሩ ደንበኞች ሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢልን በተጨማሪ በርካታ ላፕቶፖች፣ ታብሌቶች እና ሞባይል ስልኮች የእጣ ማዉጣት ሰነስርዓት በዛሬው እለት በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በይፋ ተካሂዳል፡፡

የሀገርና የትውልድ ባለውለታ የሆኑትን መምህራንና የጤና ባለሙያዎችን እንዲሁም ለደረቅና ለፈሳሽ የጭነት የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ደንበኞችን ለማክበርና ለማበረታታት ባዘጋጀው የቁጠባና ሽልማት መርሃግብር ተሳታፊ ለሆኑ ነባርም ሆነ አዳዲስ ደንበኞች ቡና ባንክ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን መሽለሙ ታውቄል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe