ቡና ባንክ የውጭ ምንዛሪ ተገልጋዮችን፤ ቆጣቢ መምህራንና የህክምና ባለሙያዎችን ሸለመ

ቡና ባንክ ላለፉት ወራት ሲያካሂድ በቆየው ሁለተኛው ዙር የመምህራን እና የጤና ባለሞያዎች “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃግብር አሸናፊ ለሆኑ ዕድለኞች እና አስረኛውን ዙር “የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ ፣ይመንዝሩ ይሸለሙ” መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ምክንያት በማድረግ የሽልማት ዕጣ ለወጣላቸው ደንበኞቹ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች  አስረክቧል።

ባንኩ ሃምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ባካሄደው በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ የ10ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ የዕጣ አሸናፊዎች ለሆኑት ዕድለኞች የ2021 የቤት አውቶሞቢል፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች ፣ ማቀዝቀዣዎች፣ የውሃ ማጣሪያዎች፣ ፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች እና ስማርት ስልኮችን በሽልማት ያበረከተ ሲሆን ለአሸናፊ መምህራን እና የጤና ባለሞያዎች ደግሞ ዘመናዊ 2021 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪናን ጨምሮ 12 ዘመናዊ ላፕቶፖች፣ 12 ታብሌቶች፣ 24 ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎች እና 6 የእረፍት ጊዜ ሽርሽር ሙሉ ወጪ የተሸፈነላቸው የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ፓኬጆችን በሽልማት አስረክቧል።

 ከባንኩ ተሸላሚዎች መሀከል ልዩ ዕድለኞች የሚገኙበት ሲሆን የአንዳንዶቹ ታሪክ ይህንን ይመስላል፤

1. ዶክተር ሜሮን ዘለቀ በሙያቸው ህዝብን የሚያገለግሉ የህክምና ባለሙያ ናቸው። ቡና ባንክ ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች ማበረታቻ ሽልማቶችን ጨምሮ በቀረጸው የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር ተሳታፊ ከሆኑ ቆየት ብለዋል። ዶክተር ሜሮን ሳያቋርጡ በመቆጠባቸው ህይወታቸውን በዕቅድ ለመምራት ከመቻላቸው በላይ ዕድል ደጃቸው ድረስ መጥታ በሽልማት አንበሽብሻቸዋለች። ዶክተር ሜሮን የ2ኛው ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር ማጠቃለያ ላይ በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ዕጣ ሲወጣ ሳያቋርጡ ቁጠባ በማድረጋቸው ብቻ የአንድ ዘመናዊ ላፕቶፕ እና ሁለት ስማርት የሞባይል ቀፎዎች በድምሩ የሶስት ሽልማቶች አሸናፊ በመሆን ሁሉንም አስደንቀዋል። በስራ ምክንያት በሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓቱ ላይ ላልተገኙት ዶክተር ሜሮን ሽልማቶቹን ለተወካያቸው አስረክቧል።

2. መምህር ስለሺ ወንድምአገኝም እንዲሁ በአንድ መርሃ ግብር የሁለት ዕጣ አሸናፊ ናቸው። “ቡና ባንክ ለመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ክብር በመስጠት በስማችን የቁጠባ መርሃ ግብር በመዘርጋቱ ብቻ ላመሰግን እወዳለሁ” ይላሉ መምህር ስለሺ። እነሆ ቡና ባንክ ለርሳቸውና ለሙያ አጋሮቻቸው በቀረጸው 2ኛ ዙር የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር ተሳታፊ በመሆን የአንድ ዘመናዊ ታብሌትና የአንድ ስማርት ሞባይል ስልክ ተሸላሚ ሆነዋል።

3. ወ/ሮ የምስራች አባተ ከውጭ የተላከላቸውን ገንዘብ በቡና ባንክ ቅርንጫፎች በመቀበላቸው ብቻ ባንካችን የሸለማቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ናቸው። ወይዘሮ የምስራች በተጠናቀቀው 10ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ ይሸለሙ መርሃ ግብር ወቅት ከወዳጅ ዘመድ ገንዘብ ሲላክላቸው ‘በቡና ላኩልኝ’ በማለታቸውና ገንዘባቸውን ለመቀበል ወደቅንጫፎቻችን ደጋግመው በመምጣታቸው ዕድል መረጠቻቸውና በአንድ መርሃ ግብር አንድ እጅግ ዘመናዊ ማቀዝቀዣና እና አንድ ስማርት የሞባይል ቀፎ ሽልማቶችን አሸንፈው ከቡና ባንክ ተረክብዋል።

4. አቶ ትዕዛዙ ነጋሽ አራተኛው የቡና ባንክ ልዩ ተሸላሚ ናቸው። አቶ ትዕዛዙ እንደወይዘሮ የምስራች ሁሉ ከውጭ የተላከላቸውን ገንዘብ በተደጋጋሚ ጊዜ በመቀበላቸውና በመመንዘራቸው ባንካችን ባዘጋጀው የ10ኛው ዙር ይቀበሉ ይመንዝሩ መርሃ ግብር የሽልማት ዕጣ ቁጥሮች ተልከውላቸው ነበር። ዕጣው በወጣበት ዕለትም አቶ ትዕዛዙ የአንድ ዘመናዊ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እና የአንድ ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎ ዕድለኛ በመሆናቸው እነሆ ሽልማታቸውን በይፋ ተረክበዋል።

ዕድለኛዋ መምህርት!!”
ላለፉት 20 ዓመታት በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ላይ አስተምረዋል። ረጅሙን ጊዜያቸውን ያሳለፉት ግን በጸሃይ ጮራ አንድኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በመምህርነት ነው። የ7 እና 8ኛ ክፍል ባዮሎጂ መምህር ናቸው። መምህርት አስናቀች አበበ።
“መምህርነት ለእኔ የተፈጠረ ሙያ ነው። ከዚህ ሙያ ውጪ ስራ ያለም አይመስለኝም” ይላሉ ለመምህርነት ያላቸውን ፍቅር ሲገልጹ።
“ትውልድን መቅረጽ፣ መሰረቱን መገንባት የመምህር ሙያ ነው። እዚያ ላይ የተበላሸ የዜጎች ግንባታ ወደላይ መውጣት ያዳግተዋል” ይላሉ።
“በማስተምርበትና በምኖርበት ሽሮ ሜዳ አካባቢ ያሉ ትምህርት ቤቶች ኢትይጵያን መመልከቻ መስኮቶች ናቸው…” ይላሉ የመምህርነት ትሩፋታቸውን ሲናገሩ።
“ከጥቂት አመታት በፊት ለመማር እየመጡ የሚበሉት ሳይኖራቸው የሚቸገሩ በርካታ ተማሪዎቻችንን በመደገፍ ነበር ደመወዛችንን የምንጨርሰው። ባዶ እጄን ቤቴ የገባሁበት ጊዜ ነበር። ችግርኛ ተማሪዎች በጓደኞቻቸው ዘንድ ዝቅ ብሎ ላለመታየት ባዶ የምሳ እቃ ይዘው መጥተው በምሳ ሰዓት ሌላ ቦታ ይቆዩና ከበሉት ጓደኞቻቸው ጋር እቃቸውን አጥበው ልክ ወደክፍል ሲገቡ ማየት በጣም ያሳቅቅ ነበር። እንዳይርባቸው ብለው ጸበል ጠጥተው የሚውሉ በርካታ ችግረኛ ተማሪዎች ነበሩ። ይህንን ችግር በመካፈል ከማስተማሩ ጎን ለጎን እነሱን የመርዳት እና የመመገብ ሰብዓዊ ሃላፊነት እኛ ላይ ነበር የወደቀው። ዛሬ ሁሉም ነገር በመስተካከሉ ደስ ብሎኛል፣ መምህርነት ለኔ ትርግሙ ይኼ ነው” ይላሉ መምህርቷ ….ሙያው ሰብዓዊነትም ጭምር መሆኑን ሲገልጹ።
መምህርት አስናቀች አበበ የቡና ባንክ ደንበኛ ከሆኑ ገና ስድስት ወራቸው ነው። “አንድ ቀን የባንኩ ሰራተኞች ወደትምህርት ቤት መጥተው “የሽልማት ማበረታቻ ያለው የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ቁጠባ መርሃግብር ተጀምሯልና ተሳተፊ” አሉኝ…..ቡና ባንክ መምህራንን አስቦ ፣ ለሙያው ክብር ሰጥቶ በስማችን የቁጠባ መርሃ ግብር በመጀመሩ ብቻ ከፍ ያለ ደስታ ስለተሰማኝ ወዲያውኑ ነበር ሂሳብ የከፈትኩት። ከዚያ በኋላም መቆጠብ ጀመርኩ።” ብለዋል።
እነሆ ሁለተኛው ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር ሲጠናቀቅና ዕጣ ሲወጣ ዕድል ወደርሳቸው ቀረበችና የ1ኛው ዕጣ የ2021 ሱዙኪ ዲዛየር መኪና አሸናፊ ሆኑ። ሽልማታቸውንም ዛሬ በግዮን ሆቴል በተካሄደው ደማቅ ስነስርዓት ከባንኩ ተቀብለዋል።
“እንዲህ አይነት ነገር በቴሌቪዠን ሳይ እውነት አይመስለኝም ነበር። እነሆ አሁን በራሴ አረጋግጫለሁ። በጣም ደስ ብሎኛል። ከሽልማቱም በላይ ቡና ባንክ ለኛ ለመምህራን በሰጠው ክብር የበለጠ ደስተኛ ነኝ። በአጋጣሚ በቅርቡ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት ትምህርት ላይ ነበርኩ። ፍቃዱን ሳገኝ መኪናዋን ለግል መንቀሳቀሻዬ እጠቀምባታለሁ። የሙያ አጋሮቼ የቡና ባንክ ደንበኛ ሆነው የቀጣዩ ዙር ተሳታፊ እንዲሆኑ እመክራለሁ። እስከፍጻሜዬ ከቡና ባንክ ጋር አብሬ እጓዛለሁ” ነው ያሉት መምህሯ።
ቡና ባንክ መምህርት አስናቀች አበበ በሙያቸው ላበረከቱት አስትዋጽዖ ያለውን ክብርና ምስጋና እየገለጸ የመኪና ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸውም እንኳን ደስ አለዎ ይላል።
3ኛው ዙር የመምህራንና ጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር በቅርቡ ይጀመራል። መምህራንና የጤና ባለሙያዎችን የዚህ መርሃ ግብር ተሳታፊ እንዲሆኑ ቡና ባንክ በአክብሮት ይጋብዛል!!
(ቡና ባንክ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe