ባለሀብቶችን ዒላማ አድርገው ሙስና ፈጽመዋል የተባሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ክስ ተመሰረተባቸው፤

በመከላከያ ሚኒስቴር በተለያዩ ክፍለ ጦር ውስጥ ያሉና የለቀቁ የሠራዊት አባላት፣ ባለሀብቶችን ዒላማ በማድረግ አጥንተውና ለይተው በማሳደድ፣ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

ክስ የተመሠረተባቸው፣ መቶ አለቃ ሀጂ ቱሉ፣ ኦፊሰር መንግሥቱ በቀለ፣ ሻምበል ሻምበል ከሀሊ፣ አሸናፊ ወልደ ሰማያት፣ ሹምበዛ ፍቃዱ፣ አዲስ ዓለሙ፣ ከመከላከያ የለቀቁና በሌሉበት የተከሰሱ ተስፋዬ ለሚ  እና ሻለቃ ዱጉማ ናቸው፡፡

ተከሳሾቹ በቡድን በመደራጀት የማይገባ ብልፅግና ለማግኘትና ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ፣ ሰሌዳ ቁጥር ያለጠፈ የመከላከያ መኪና ይዘው ውንብድና መፈፀማቸው በክሱ ተጠቅሷል፤

ተከሳሾቹ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ስልጤ ሠፈር በሚኖሩት ተበዳይ አቶ አብዱል በርናምስ መኖሪያ ቤት በመሄድ ግለሰቡን ከቤታቸው እንዲወጡ አድርገው በያዙት የመከላከያ መኪና ውስጥ ካስገቧቸው በኋላ፣ በሕገወጥ መንገድ ‹‹ስኳር፣ ዘይትና መሣሪያ ትሸጣለህ፡፡ እንድንለቅህ አምስት ሚሊዮን ብር ክፈል፤›› በማለት መደራደራቸውን ተመልክቷል፤

፣ ነገር ግን ተበዳዩ የተጠየቁትን ያህል ገንዘብ መክፈል እንደማይችሉ ገልጸው፣ 700,000 ብር ለመክፈል ተስማምተው በተለያዩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ዳሸን ባንክ በተከፈቱ የቁጠባ ሒሳብ ቁጥሮች  ክፍያ መፈጸማቸውን ክሱን የመሠረተው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ በድርጊታቸው በመቀጠል ሃና ማርያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ ከሆኑት አቶ ሙሉጌታ ታደሰ ብር 300 መቶ ሺ እንዲሁም ወ/ሮ አዜብ በርሔ ከተባሉ ግለሰብ ብር 115 ሺ ብር አላግባብ መቀበላቸውን በመጥቀስ ሥልጣንን አላግባብ መገልገል ከባድ የወንጀል ክስ ተከሰው፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሙስና ወንጀሎች ችሎት  ቀርበዋል፡፡

ችሎቱ ጉዳዩን በመመርመር ብይን ለመስጠጥ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ሪፖርተር ዘግቧል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe