“ባለፋት አራት ዓመታት በተደረገ የመካንነት ህክምና 47 በመቶ ስኬታማ ሆኗል”- የቅዱስ ጳውሎስ የስነተዋልዶና መካንነት ተቋም

ባለፋት አራት አመታት በተደረገ የመካንነት ህክምና 47 በመቶ ስኬታማ መሆኑን የቅዱስ ጳውሎስ የስነተዋልዶና መካንነት ተቋም አስታወቀ።

የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅና የዘርፉ ሰብስፔሻሊስት ዶ/ር ቶማስ መኩሪያ ለFM 97.1 እንደተናገሩት፣ ቴክኖሎጂ አገዝ የመካንነት ህክምና(in vitro fertilisation) ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 5ሺህ 500 ጥንዶች ህክምናውን ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህ ውስጥ 47 በመቶ ህክምናው ስኬታማ ሆኖ መውለድ የቻሉ ናቸው ብለዋል ዋና ስራ አስኪያጁ።

ዓለም በደረሰበት የህክምና ደረጃ መሰረት ይህ አይነቱ የመካንነት ህክምና ከ 30 እስከ 57 በመቶ ውጤት ከተገኘበት በስኬታማነት እንደሚጠቀስ ተጠቁሟል።

ውጪ ሀገር ሄዶ ለመታከም እና ለመውለድ በአማካይ 10 ሺህ ዶላር ይፈጃል ያሉት ዶ/ር ቶማስ፤ “በአጠቃላይ እስካሁን በሀገር ውስጥ ባደረግነው ህክምና 55 ሚልዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አድነናል” ብለዋል።

አሁን ላይ የእንቁላል ልገሳ፣ የማህፀን ውሰት እና የወንድ ዘረመል ልገሳ ህግ ባለመኖሩ በዚህ ችግር የተጋለጡ ዜጎች ለእንግልትና ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ህጉ በሀገሪቱ ባለመኖሩ ምክንያት በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይህንኑ ህክምና ለማግኘት ከ 3 ሺህ በላይ መካኖች ወደ ውጪ ለመላክ ተገደናልም ነው ያሉት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe