ባራክ ኦባማ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ በሆነ ወጪ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ገዙ

የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዚዳት ባራክ ሁሴን ኦባማ ከስልጣን ከወረዱ ከ5 ዓመታት በኋላ እጅግ ቅንጡ የተባለ መኖሪያ ቤት መግዛታቸው ተሰማ፡፡ ፕሬዚዳት ኦባማ ከባለቤታቸው ሚሼል ጋር ተማክረው ገዙት የተባለው መኖሪያ ቤት በማሳቹሴት የሚገኝ ሲሆን ሰባት ዘመናዊ መኝታ ክፍሎችና ዘጠኝ መፀዳጃ ክፍሎችን ይዟል ተብሏል፡፡

ኦባማ የገዙት መኖሪያ ቤት 11.75 ሚሊየን ዶላር በአሁን የኢትዮጵያ ምንዛሪ 587 ሚሊዮን ብር ዋጋ የወጣበት ሲሆን በውሃ ዳርቻ የሚገኝ ነው፤ በሁለት አቅጣጫ የባህሩን ንፋስ በረንዳ ላይ ሆኖ መቀበል ይቻላልም ተብሏል፡፡የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች በስልጣን ላይ ሳሉ ከከተማ ወጥተው በባህር ዳርቻዎች የማሳለፍ ልምድ ያላቸው ሲሆን ከስልጣን ከወረዱ በኋላ በእንዲህ አይነት የባህር ዳርቻ ቋሚ መኖሪያ ቤት የገዙት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ስለመሆናቸው ማልሰን ግሎብ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe