ባንኮች በአስገዳጅነት የቦንድ ግዥ እንዲፈጽሙ የሚያደርጋቸው መመሪያ ከመጭው ሰኔ ወር ጀምሮ ሊነሳ መሆኑ ተሰማ፡፡
ውሳኔው የባንክ ኢንዱስትሪውን ሊያነቃቃ የሚችል እንደሚሆንም ተመላክቷል፡፡ ብሐየራዊ ባንክ አስገዳጅ የቦንድ ግዥና የብደር ጣሪያ መመሪያዎች ሊነሱ መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡
እነዚሁ አስገዳጅ መመሪያዎች በመጪዎቹ ሰኔ እና መስከረም ወር ላይ ሙሉ በሙሉ እንደሚነሳ የብሐየራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል፡፡
ላለፉት 2 ዓመታት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ጣሪያ ገደብ በመስከረም ወር ላይ ይነሳል መባሉ ነው የተሰማው፡፡ የመመሪያዎቹ መነሳት የፋይናስ ዘርፉን ለማሻሻል ከሚወሰዱት ቀጣይ እርምጃዎች መካከል እንደ ሚካተቱ ዋና ገዥው ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡
ውሳኔው ባንኮች ለረጅም ዓመታት በአስገዳጅነት ቦንድ ሲገዙበት ከነበረው ሁኔታ ለውጥ እንደሚያመጣ ይታመንበታል፡፡
ከዚህ ቀደም ባንኮች ከሚሰጡት ብድር 27 በመቶውን ለልማት ባንክ ቦንድ ግዥ እንዲያውሉ ይገደዱ ነበር፡፡

