ባንኮች በከተማ አስተዳደሩ የወጣው የምሽት ስራ ተቃወሙ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እስከ ምሽት 3፡30 አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ክፍት እንዲሆኑ የሚለውን መመሪያ ነው ከስራችን ጋር አይጣጣምም ያሉት፡፡

የባንኮች ማህበር ባንኮች በዚህ ወቅት በቴክኖሊጂ ምክኒያት የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶችን ለደንበኞች በቀላሉ እያቀረቡ ስለሆነ የምሽት አገልግሎት አላስፈላጊ እና አግባብነት የሌለው ነው ብሏል፡፡

ማህበሩ ደንበኞች በኤቲኤም እና በፖስ ማሽኖች እና በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ደንበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት ስለሚችሉ ባንኮች እስከ ምሽት ክፍት ሆነው መቆት አለባቸው የሚለው አስገዳጅ መመሪያ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጻል፡፡

በተጨማሪም ማህበሩ በፌደራል መንግስት ስር ያሉ ተቋማትን የከተማ አስተዳደሩ በመመሪያ እንዲያስተዳድር የተሰጠው ስልጣን አግባብ እንዳልሆነ እና መመሪያው ከመውጣቱ በፊት የኢትዮጽያ ብሔራዊ ባንክ አስተያየት መጠየቅ ነበረበትም ብሏል፡፡

መመሪያው የባንኮችን የስራ ባህሪ ያላገናዘበና ለባንኮችም ሆነ ለደንበኞች ደህንነት አስጊ ሊሆን እንደሚችል መግለጹን መነኸሪያ ሬዲዮ ዘግቧል፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe