ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጠየቀው በጀት ከባለፈው ስምንት እጥፍ ይልቃል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በሚቀጥለው አመት ይካሔዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ለሥራ ማስኬጃ መጠየቁን አስታወቀ። ምርጫ ቦርዱ ይኸን ያስታወቀው በአዲስ አበባ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

በሚቀጥለው አመት ለሚካሔደው ምርጫ የሥራ ማስኬጃ አራት ቢሊዮን ብር ቢጠይቅም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት «እንዲከለስ» በመታዘዙ ወደ 3.7 ቢሊዮን ብር ዝቅ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮምዩንኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ወይዘሪት ሶሊያና እንዳሉት ከዚህ ውስጥ 900 ሚሊዮን ብር ከአጋር ድርጅቶች እና ከውጪ እገዛ ለማሟላት ታቅዷል።

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በተያዘለት መርሐ-ግብር መሠረት ሊካሔድ ይገባል አሊያም ይራዘም በሚል ለሚወዛገቡበት ምርጫ የተጠየቀው የገንዘብ መጠን ከባለፈው ምርጫ አኳያ ስምንት እጥፍ ይልቃል። ወይዘሪት ሶሊያና ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ በታቀዱ ሥራዎች ምክንያት የገንዘብ መጠኑ መጨመሩን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባለፉት ስድስት ወራት የሠራቸውን አበይት ጉዳዮች ዘርዝሯል። ወይዘሮ ሶሊያና እንዳሉት የሕግ ማዕቀፎች እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፎች እና ውይይቶች ማድረግ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ባለፉት ስድስት ወራት ካከናወናቸው መካከል ይገኙበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር እንደሚሰጠን ቃል የገባልንን መኖሪያ ቤት ሊያስረክበን ባለመቻሉ እና የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የፖለቲካ ወገንተኝነት ያለበት መብታችንን የማያስጠብቅና የማይወክለን ነው በሚል ትናንት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል። 1200 የሚሆኑ መምህራን መስቀል አደባባይ በመውጣት ለሰዓታት ጥያቄያችንን ለማሰማት መሞከራቸውን አንድ የታሪክ አስተማሪ ተናግረዋል። አብዛኛው መምህር መዋከቡንና አላማውን ለማሳካት ሳይችል መመለሱን የተወሰኑ መምህራንም ለግማሽ ቀን ታስረው መፈታታቸውን ገልጸዋል።

መምህራኑ ከደሞዝ በላይ የመኖሪያ ቤት አንገብጋቢ ችግር እንደሆነባቸውና ይህንንም በተደጋጋሚ ጠይቀው ምላሽ ማጣታቸውን ይልቁንም ለዘመናት በአፈና ፣ በአካዳሚክ ነጻነት እጦትና በኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ ማሳለፋቸውን የሰልፉ ተሳታፊ አውስተዋል።

በመላ ሃገሪቱ ከ508 ሺህ በላይ አባላቶች አሉኝ የሚለው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የመምህራን የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታ ከ 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ፓኬጅ ጸድቆ ተግባራዊ የሆነ ሲሆን በዚህም ከ 50 ሺህ በላይ መምህራን በዚህ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራሁ ነው ብሏል።

በ2009 ዓ.ም. መምህራንን ያላካተተው የደሞዝ ጭማሪም መልስ እንዲያገኝ እየሰራሁ ነው ብሏል። የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሃንስ በንቲ መምህራኑ እያነሱ ያሉት ጥቄቃ ተገቢ ቢሆንም አካሄዱን ግን እኛ አናውቀውም የትላንቱ ሰልፍ ላይም ታሰሩ ስለተባሉ ሰዎች የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል።

በትናንቱ የመስቀል አደባባይ ድምጽን የማሰማት እንቅስቃሴ ላይ ከተገኙት ይልቅ በፖሊስ ተከልክለው የቀሩት እንደሚልቁ የሰልፉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። ስለጉዳዩ ለማጣራት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ሙከራ ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም።

Source: mereja

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe