ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎቶችን ለመስጠት ፍቃድ ያገኙ 90 ድርጅቶችን ይፋ አደረገ

ብሄራዊ ባንክ፣ በአገሪቱ ውስጥ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎቶችን ለመስጠት ፍቃድ ያገኙ ድርጅቶችን ዝርዝር ዛሬ ኅዳር 3 ቀን ይፋ አድርጓል። ባንኩ፣ ለገንዘብ አስተላላፉነት አገልግሎት ከ90 በላይ ድርጅቶች ሕጋዊ ፍቃድ እንዳገኙ ገልጧል። ባንኩ፣ ቀደም ሲል ታግዶ የነበረው መቀመጫውን በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት ያደረገው ረመዳ ፔይ የተባለው ድርጅት፣ አስፈላጊው የቁጥጥርና የክትትል ሥራ ከተሠራ በኋላ እገዳው ተነስቶለት በገንዘብ አስተላላፊነቱ እንዲቀጥል መፍቀዱንም አስታውቋል።

ረመዳ ፔይ እና ሌሎች ሦስት አሜሪካ የሚገኙ ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች “በገንዘብ አጠባ” እንደተሠማሩ በመግለጽ፣ በድርጅቶቹ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ ገንዘብ ሊወረስ እንደሚችል ባንኩ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ባንኩ በረቡዕ’ለት መግለጫው፣ ከገንዘብ አስተላላፊነት የታገዱ ድርጅቶች በሙሉ በኢትዮጵያ ሕጎች እና ደንቦች መሠረት መስፈርቶችን ለማሟላት ማስተካከያ ርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስቧል። [ዋዜማ]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe