ብሔራዊ ባንክ የ70 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ለግል ባንኮች በማውጣት አጫርቷል፡፡ የዛሬውን ጨምሮ ለሦስተኛ ጊዜ ነው በዚህ ዓመት ባንኩ ዶላርን ለባንኮች በጨረታ መልክ ያቀረበው፡፡
ከዚህ ቀደም የካቲት 18 /60 ሚሊዮን ዶላር መጋቢት 23 ደግሞ 50 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የካቲት ላይ በወጣው ጨረታ አንድ የአሜሪካን ዶላር በአማካኝ 135 ብር የተሸጠ ሲሆን፤መጋቢት 23 በነበረው ደግሞ የተወሰነ ቅናሽ አሳይቶ በአማካኝ 131.7 ብር ተሽጦ ነበረ፡፡ በትላንትናው እለትም አንድ የአሜሪካን ዶላር በአማካኝ መጋቢት ላይ በከበረው ጋር ተቀራራቢነት አሳይቶ በ131.49 ብር ተሸጧል፡፡ በጨረታውም 26 ባንኮች ተሳታፊዎች እንደነበሩ ተሰምቷል፡፡ በጨረታውም 26 ባንኮች ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጻል፡፡
ብሔራዊ ባንክ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በየ አስራ አምስት ቀኑ ተመሳሳይ ጨረታ እያወጣ እንደሚቀጥል መግለጹ ይታወቃል፡፡ ባንኩ እስከ ሰኔ 30 ድረስ በየ አስራ አምስት ቀኑ ዶላር በጨረታ እያቀረበ የሚቀጥል ከሆነ ገበያውን ማረጋጋት ላይ ሚና እንደሚኖረው በባለሙያዎች ዘንድ ይነገራል፡፡
የብሔራዊ ባንክ የዶለር ጨረታ የግል ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡትን የውጭ ምንዛሬ ከፍ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ይህም ገበያውን ከማረጋጋት አኳያ ሚና ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡

