ብሔራዊ ባንክ የዉጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን ገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የዉጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አዉጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ አስታዉቋል።
የዉጪ ምንዛሪ ገበያ ዉስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች በግላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላት እንዲሰሩ ተደርጓል።
ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ክትትልና መጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱፈራ እንደተናገሩት ” የዉጪ ምንዛሪ ዚሮዉን ለመክፈት ፍላጎት አሳይተዋል ያላቸዉን ሰዎች መቀበሉን ” የገለፁ ሲሆን ከንግድ ሚኒስትር ጋር ያለዉ ጉዳይ ከተፈታ ወዲያው ፍቃድ መስጠት እንጀምራለን በእኛ በኩል ሁሉም ነገር አልቋል ሲሉ ተደምጠዋል ።
እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለፃ “ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖሩ የዉጪ ሀገር ዜጎችም አካዉንት ከፍተዉ ሲፈልጉ ብቻ ወደ ብር ቀይረዉ እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል ” ይህም በድፍረት የተደረገ ነዉ ማለት ይቻላል ሲሉም እርጃዉን አድንቀውታል።
ሀገር ዉስጥ ያሉ ማንኛውም የዉጪ ምንዛሪ የሚያገኙ ግለሰቦች በትንሹ በ 100 ዶላር የዉጪ ምንዛሪ አካዉንት መክፈት እንደሚችሉ የጠቆሙት አበባየሁ ዱፈራ ይህ ጥቅሙ ለግለሰቦች ሳይሆን ሀገርም ጭምር ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe