ብሪክስ የአሜሪካን ዶላርን የሚተካ የክፍያ ሥርዓት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተነገረ

የብሪክስ አባል ሀገራት በአለም አቀፍ ንግድ ላይ የአሜሪካን ዶላር የበላይነትን ለመገዳደር አዲስ የክፍያ ሥርዓት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በቅርቡ ይፋ አድርገዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንደተናገሩት ይህ አዲስ የክፍያ ዘዴ ከባህላዊው ሥርዓት ፈጽሞ የተለየ ሲሆን በአለም አቀፍ የፋይናንስ ገበያዎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።
በተለይም የአሜሪካ ዶላር በአለም አቀፍ የንግድ ልውውጦች ውስጥ ምንም ዓይነት ሚና እንደማይኖረውና አብዛኛዎቹ የንግድ ስምምነቶች በአባል ሀገራቱ የገንዘብ ምንዛሬዎች እንደሚፈጸሙ ይጠበቃል።
ሚኒስትሩ አክለውም ይህ አዲስ የክፍያ ሥርዓት ከብሪክስ አባል ሀገራት ውጭ ላሉ ሀገራትም ክፍት እንደሚሆን አረጋግጠዋል። ይህም ማለት ማንኛውም ሀገር የአሜሪካን ዶላር ሳይጠቀም የንግድ ልውውጦችን ማከናወን ይችላል ማለት ነው።
በተጨማሪም ይህ አዲስ የክፍያ ሥርዓት በአሜሪካና በአውሮፓ ቁጥጥር ሥር ባለው የ ስዊፍት የክፍያ ሥርዓት ላይ እንደማይመሰረትና ይልቁንም ከውጭ ተጽዕኖ ነፃ የሆነ የራሳቸውን የክፍያ መድረክ ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ አዲስ የክፍያ ሥርዓት በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ የአለም አቀፍ ንግድ አፈጻጸም ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።
ይሁን እንጂ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መንበረ ስልጣናቸውን በተቆጣጠሩ ማግስት የብሪክስ ቡድን የአሜሪካን ዶላር የሚፎካከር ገንዘብ ቢፈጥር 100% ቀረጥ እንደሚያስከፍሉ በማስጠንቀቅ ምላሽ ሰጥተዋል።
ትራምፕ እንዳሉት “የብሪክስ ሀገራት ዶላርን ትተው ለመንቀሳቀስ እየሞከሩ ነው የሚለው ሀሳብ ዝም ብለን የምንመለከተው አይደለም” ብለዋል።
ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ ብራዚል፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኢራን፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የዚህ ህብረት አባል መሆናቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe