ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ለጊዜው እንዳይበርሩ እገዳ ተጣለባቸው

የቦይንግ ኩባንያ 777 አውሮፕላኖቹ የሞተር ስሬታቸው 4000-112 የሆኑት በመላው አለም ለጊዜው እንዳይበርሩ አሳሰበ።
ኩባንያው ማሳሰቢያውን የሰጠው በአሜሪካ ዴንቨር ላይ ቦይንግ 777 ስሬት በሆነ አውሮፕላን ሞተር ላይ አደጋ መፈጠሩን ተከትሎ ነው፡፡
ባለፈው ቅዳሜ 231 ተሳፋሪዎችን የጫነው ይኸው የአውሮፕላን ስሬት በሞተሩ ላይ የገጠመውን ችግር ተከትሎ ተመልሶ ለማርፍ መገደዱን የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር አስታውቋል።
ይህን ተከትሎም የቦንግ 777 ስሬት የሆነን አውሮፕላን የሚጠቀሙ እንደ ዩናይትድ እና ጃፓን ያሉ አየር መንገዶች ለጊዜው 62 አውሮፕላኖቻቸውን ከበረራ ውጭ አድርገዋል።
ሌሎች አየር መንገዶችን ጨምሮ ተመሳሳይ ሞተር የሚጠቀሙ የዚሁ ዓይነት የሆኑ 128 አውሮፕላኖች መብረር እንደሌለባቸውም ቦይንግ አስታውቋል።
ችግር አለበት በሚል እንዳይበር እየተደረገ ያለው ቦይንግ 777 አውሮፕላን ላይ 4000-112 ሞተር ስሬት ያላቸው አውሮፕላኖችን የሚጠቀሙት የአሜሪካው ዩናይትድ፣ ሁለት የጃፓን እና አንድ የደቡብ ኮሪያ አየር መንገዶች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ የችግሩ ምንጭ እስኪታወቅ በረራዎች እንዲቆሙ ሲል የአሜሪካ ፌደራል አቪዬን አስተዳደር ለጊዜው ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል።
በዚህ አውሮፕላን ዓይነት ከዚህ ቀደም ተደጋጋሞ አደጋዎች ገጥመውት እንደነበርም ተመልክቷል።
ምንጭ፤ቢቢሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe