ተራዝሞ የነበረው በአፍሪካ ሕብረት የሚመራው የሰላም ንግግር ከ4 ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ቀን እንደተቆረጠ ተሰማ

ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከ4 ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ቀን እንደተቆረጠለት ተሰምቷል።

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የነበረውና በሎጅስቲክስ ዝግጅት ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከዛሬ 4 ቀናት በኃላ (ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ/ም) በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ መሆኑ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን ለማድረግ ለጥቅምት 14/2015 ዓ/ም ቀን መቁረጡን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ፤ ” በዚሁ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናችንን በድጋሚ አረጋግጠናል ” ብለዋል። ” ነገር ግን መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን የመከላከል ርምጃ ለማጠልሸት የሃሰት ከስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አካካት ላይ ያለውን ቅሬታ ይገልፃል።” ሲሉ አክለዋል።

አፍሪካ ህብረት በህብረቱ የሚመራና በደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ የሰላም ንግግር ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለህወሓት ግብዣ አቅርቦ እንደነበርና በሁለቱም በኩል ግብዣው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።

የሰላም ንግግሩ ፤ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ እንደሚመራም መገለፁ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe