ተቋርጦ የነበረዉ የባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ ዉድድር ( ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ) ሊካሄድ ነዉ!

በኢትዮጵያ ለተከታታይ 3 ዓመታት ሲካሄድ የነበረዉና ለቡና አርሶአደሮች ከ 3 ሚሊዮን በላይ ዶላር ገቢ ያስገኘዉ የባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ ዉድድር ( ካፕ ኦፎ ኤክሰለንስ) ለአንድ ዓመት ተቋረጠ በኃላ በድጋሚ እንደሚጀመር ተነግሯል።ከ2020 ጀምሮ በኢትዮጵያ የጀመረዉ ዉድድሩን አዘጋጅ የሆነዉ አልያንስ ፎር ኮፊ ኤክሰለንስ በየካቲት ወር መጀመሪያ ባወጣዉ መግለጫ “የዘንድሮን (2023) ዉድድር ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና ከብሔራዊ የቡና ማህበር ጋር ዉይይት ቢደረግም ባለስልጣኑ ዉድድሩ ለ 2024 መተላለፉን” ገልጿል።

በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ ነበር የተባለዉ የባለልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር በኢትዮጵያ በድጋሚ ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት “በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር እንዲሁም በአሊያንስ ፎር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ መካከል” በዛሬው ዕለት መፈረሙን ካፒታል ሰምቷል።ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በአዘጋጁ አገር በጥራታቸው የላቁ አሸናፊ ቡናዎችን ውድ በሆነ ዋጋ በግልፅ ጨረታ የሚሸጥ የጥራት ውድድር እ.አ.አ 1999 በብራዚል የተጀመረ ሲሆን ባለፉት 24 አመታት በ 11 ቡና አምራች ሀገራት ተካሄዶዋል፡፡

ዉድድሩን የሚመራው አሊያንስ ፎር ኮፊ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ በአሜሪካን ሀገር የሚገኝ ደርጅት በጥራታቸው የላቁ ልዩ የሆኑ ቡናዎችን ለመምረጥ የሚያስችል አካሄድና ዘዴ መፍጠር መቻሉ ይነገራል።በዚህም ተወዳዳሪ ቡናዎች በተለያየ ደረጃ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የቡና ቀማሾች ተቀምሰው የላቁና ባለልዩ ጣዕም የሆኑ ቡናዎች በአሸናፊነት ይመረጣሉ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe