” ተኩስ አቁሙ ተጥሷል ” የኢራን መገናኛ ብዙኃን

የኢራን መገናኛ ብዙኃን በሰሜናዊ ኢራን ፍንዳታዎች በመሰማታቸው ” ተኩስ አቁሙ ተጥሷል ” አሉ።

በኢራን እና በእስራኤል መካከል የተኩስ አቁም መደረጉ ቢነገርም በሰሜናዊ ኢራን ማዛንዳራን ግዛት ውስጥ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ለኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ ቅርብ የሆነው ‘ፋርስ’ የተባለው የዜና ወኪል እንዳለው ከዋና ከተማዋ ቴህራን በስተሰሜን ማዛንዳራን ግዛት ውስጥ በምትገኘው ባቦልሳር ከተማ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፊል መንግሥታዊ የሆኑት ‘መህር’ እና ‘ኢስና’ የተባሉት የዜና ወኪሎች በሰሜናዊ ግዛት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች ፍንዳታዎች መከሰታቸውን እና የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ተኩስ መሳማቱን በመጥቀስ የተኩስ አቁሙ “ተጥሷል” ብለዋል።

በተጨማሪም የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ፍንዳታዎች መከሰታቸውን እና የግዛቲቱን አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ ክስተቱን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች ገና አለመታወቃቸውን መናጋራቸው ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ” እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም የለባትም ” በማለት ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቱ  ” እስራኤል፤ እነዚያን ቦምቦች አትጣይ። በጥቃቱ የምትቀጥይ ከሆነ ከፍተኛ ጥሰት ነው። የጦር አውሮፕላን አብራሪዎችሽን አሁኑኑ ወደ ቤታቸው መልሺ! ” ብለዋል።

ይህ የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ የመጣው ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የተኩስ አቁም በኢራን እና በእስራኤል መካከል መደረጉን ካስታወቁ በኋላ ነው።

እስራኤል በትራምፕ ሃሳብ መስማማቷን ስታሳውቅ፣ ኢራን ደግሞ ጥቃቱን የምታቆመው እስራኤል ካቆመች ብቻ ነው ብላለች።

ምንጭ ፦ ቢቢሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe