ተወዳጇ የሶል ንግሥት አስቴር አወቀ የ2017 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ በሙዚቃ ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች::

በመላው ዓለም የኢትዮፒያን ሙዚቃ ተሰሚነት ከፍ ስላደረግሽ ምስጋናችንን እያቀረብን የ2017 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚ በመሆንሽ ደስታችን የላቀ ነው::
አሰላ በ1951 ተወለደች ጥቂት ጊዜ እዛ አሳልፋ ወደ ጎንደር ሄደች እዛም ትንሽ ቆይታ አዲስአበባ መጣች አዲስ አበባ መጥታ ፖሊስ ኦኬስትራ ባንድ ሄዳ ስትወዳደር ድምጽሽ አያምርም ብለው ጣሏት።
ከዛ በ13 አመቷ ሃገር ፍቅር ቴአትር በተወዛዋዥነት እና በድምጻዊነት ተቀጠረች ከዛማ ከተለያዮ ባንዶች ጋር መስራት ቀጠለች አብራ የሰራቻቸው ባንዶች ኮንትኔታል ባንድ፣ ሆቴል ዲአፍሪክ ባንድ፣ሮሀ ባንድ፣ አይቤክስ ባንድ እና ዋቢ ሸበሌ ባንድ ጋር የተለያየ ዝግጅቶችን አቅርባለች።
በወቅቱ የብዙነሽን ከሃገር ውስጥ ከውጪ ደሞ donna summer ፣aretha franklin እና የሌሎችን ትጫወት ነበር ታዲያ በዚህ መሐል የሐይሉ መርጊያ «ቼበለው ቼ» ሸክላ ሲዲ ሲሰራ ለአጃቢነት ሄዳ ስትሰራ አሳታሚው አሊ ታንጎ ያያታል።
የታንጎ ሙዚቃ ቤት ባለቤት እናም ይቺ ልጅ ድምጿ ጥሩ ነው ትልቅ ደረጃ ትደርሳለች የሰው ስራ ብቻ መስራት የለባትም ይልና የራሷን ስራ እንድትሰራ ያረጋል ከውብሸት ፍሰሀ ጋር አብሮ አሰራት ከዛም ለብቻዋ መስራት ጀመረች ህዝቡም እየተቀበላት እየወደዳት መጣ።
እሷም ስራዋን እያከታተለች መስራት ያዘች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነቷ እየጨመረ መጣ ስለፍቅር ስትዘፍን ያፈቀረች እንጂ እየዘፈነች አይመስልም የምትለውን ድምጿ ውስጥ ሆናው ይታያል ሙዚቃዎቿን ከሰማህ ብቻ ፍቅር ይይዝሀል ይዞህም ከሆነ ይብስብሀል አያሌ ስራበዎችን ሰርታለች ታዲያ በየዘፈኖቿ የድምጿ ማማር አጃኢብ ያስብላል ሙናዬ የሚል ተወዳጅ አልበም ሰርታ ወደ ሃገረ አሜሪካ ተጓዘች እዛም ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የተለያዩ የሐበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ስራዋን ታቀርብ ነበረ ከዚህ እነ ሶስና ታደሰ፣ ይልማ ገ\አብ እና ሌሎች ግጥምና ዜማ እየሰሩ ይልኩላት እና አልበም ትሰራ ነበር።
አሜሪካን ሃገር ድምጽት ት\ቤት ሄዳ አንቺንማ ልናስተምር ችልም እንደውም ለተማሪዎቻችን አስተምሪልን ተብላ አስተምራለች ሙዚቃዋ ቢልቦርድ ላይ ለ10 ሳምንት ማስቀመጥ የቻለች አለም አቀፍ ድምፃዊት ናት ለብዙዎችም ተምሳሌት ሆና የምትታይ በቀለም ትምህርቷ ሰቃይ ተማሪ ነበረች ዶክተር መሆን ነበር የምትፈልገው ዛሬ ታዲያ የሚሊዮኖችን ልብ በፍቅር ታክማለች።
ድምጿ እያደር እንደ ወይን እየጣፈጠ የሚመጣላት ስለፍቅር፣ ስለ አንድነት፣ ስለሀገር ዘፍና የማትጠግበው ሁሌም መገለጫዋ ፍቅር የሆነው ተወዳጇ የሶል ንግስቷ አስቴር አወቀ!!!
አስቴር ሁሌ ስሰማው የምገርምበት ማስተር ፒሷ ከምላቸው አልበሟ መሐል ሀገሬ አልበም ነው በሁሉ ነገሩ ሙልት ጥቅቅ ያለ ስራ ነው የአልበሙ መጣሪያ የሆነው ራሱ ሀገሬ የሚለው ስራዋ እንኳን ተሰደህ ሀገር እያለህ ብትሰማው አንዳች ደርሶ የሚወር ስሜት ይሰማሀል።
“ይሄም ሀገር ሀገር ይላል ሀገር ይሄ ሀገረ ብርቁ
እኔም ሀገር ሀገር ሀገር አለኝ ሀገር የሚታይ በሩቁ….”
ከ47አመት በላይ ከነተወዳጅነቷ መዝለቅ የቻለችው ይቺ ተወዳጅ ኮኮብ ስለ አበርክቶትሽ በሙሉ እጅ እንነሳለን አስቱካ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe