ተወዳጇ ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ አዲስ አልበም ይዛ እየመጣች መሆኑ ተሰማ።
ድምፃዊት ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ አዲሱን አልበሟን ማጠናቀቋን ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግራለች።
”ደህና ሰው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አልበም አስፈላጊው ስራው ተጠናቆ ለመቅረብ ዝግጁ ሆኗል ብላለች።
ስለ አልበሙ ዝርዝር መረጃ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግም ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ከድምፃዊቷ መስማቱን ገልጾ ዘግቧል።
ፍቅርአዲስ ነቃ ጥበብ በ2008 ዓ/ም ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ ያደረሰችው “ምስክር” የተሰኘ አልበሟን እንደሆነ ይታወሳል።//

