“ተዘጉ የተባሉ ኤምባሲዎች ዝርዝር ጉዳይ ውሸት ነው”- አምባሰደር ዲና ሙፍቲ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች ላይ ፍተሻ ይደረጋልም ብሏል።

የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔው ቡድኑ የደህንነት ስጋት አለመሆኑ ተከትሎ የተወሰነ መሆኑንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ወደትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻ እና ምርመራ እንደሚደረግ አስታወቀ።

የሚኒስቴር መ/ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። አምባሳደሩ ለትግራይ ክልል ለሚደረገው የሰብአዊ እርዳታ የአለም አቀፍ ተቋማት የበረራ ፍቃድ ቢሰጥም፤ እያንዳንዱ በረራ ግን መነሻው ከአዲስ አበባ እንደሆነ ገልፀዋል።

ለሰብዓዊ እርዳታ በሚል ወደትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚገደርግ አስረድተዋል።

እያንዳንዱ በረራ አዲስ አበባ ካለፈ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል እንደሚሄድ እና ሲመለሱም አዲስ አበባ አርፈው መሄድ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።“አንፈተሽም ያለ ካለ ባይመጣ ይሻላል”ም ብሏል አምባሳደሩ፡፡

አምባሳደሩ የትላንትናው የፀጥታው ምክር ቤት ስበሰባ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የልማት እና አፍሪካዊ ጉዳይ መሆኑን ያረጋገጠ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው ብለውታል፡፡በምክርቤቱ ተለዋጭ እና ቋሚ አባል ሀገራት ጋር በተናጠል የተሰራው የማስረዳት ስራ ፍሬ ማፍራቱን ያሰየ ስብሰባ ነበርም ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፡፡

ከስብሰበው አስቀድሞ የተቃውሞ ሃሳባቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማሳየት መሞከራቸውም ቀጥተኛ ያልሆነ የራሱ ተፅእኖ የነበረው መሆኑን እና ኢትዮጵያውያኑ ያላቸውን ሀገር ወዳድነት ያሳዩበት ነው ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በትግራይ የተወሰደውን የተጠናጠል ተኩስ አቁሙ ምክንያት በተመለከተ በውች ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለአምባሳደቶችና ለአለምአቀፍ ተቋማት ተወካዬች ማብራሪያ መሰጠቱን አስታውሷል።

የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ላይ የተደረሰው ህዝቡ የግብርና ስራውን በተረጋጋ መንገድ መከወን እንዲችልና ቡድኑ የደህንነት ስጋት አለመሆኑ ተከትሎ እንደሆነም ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ሶሞኑን ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ንግግራቸው ከኤምባሲዎችና አጠቃላይ ዲፕሎማሲ ስራዎችን በተመለከተ ያነሱትን ነጥብ ተከትሎ በተለያዩ የትስስር ገፆች ሲራገብ የነበረውን የ”30 ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ሊዘጉ ነው” ወሬን ከእውነት የራቀ እንደሆነም አስረድቷል፡፡

አምባሳደር ዲና “ተዘጉ የተባሉ ኤምባሲዎች ዝርዝር ጉዳይ ውሸት ነው”ም ብለዋል፡፡ የዲፕሎማቶችን ጥሪ በሚመለከት ከሆነ የተለመደ አሰራር መሆኑንና አዲስ ነገር አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደሌሎች ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች ሁሉ፤ የተቋም ሪፎርም እየተደረገ መሆኑንና በሂደት የሚኖሩ ለውጦች ካሉ ይፋ እንደሚደረገም ቃል አቀባዩ ተናግሯል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe